የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ተደራራቢ በደሎች ሲፈፀሙ እንዳላየ ያለፈው ምክር ቤት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የከተማዋን ዲሞግራፊ ለመቀየር በተጠና መልኩ እየሰራን ነው ሲሉ ክቡር ሚኒስቴሩ ያንንም በሰዎቻቸው አማካኝነት መሬት ላይ አውርደው ተፈፃሚ ሲያደርጉ ድምፅ ያላወጣው ምክር ቤት።

በሜንጫና ገጀራ ታጅበው አዲስ አበባን ለማተራመስ ቀን ለሊት እየተጉ ያሉ ቡድኖች በግልፅ አቋማቸውን ሲገልፁ እንዲሁም በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ በፌደራል ፖሊስ ታጅበው አልተሳካላቸውም እንጂ ጥቃት ለመሰንዘር ሲሞክሩ እንቅልፍ ላይ የነበረው ምክር ቤት።

ዛሬ የከተማው ህዝብ ተደራጅቶ በፍፁም ሰላማዊ መንገድ ሃሳቡን ቢያቀርብ ድምፁን ሰምተነው የማናውቀው አዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬም እንደ ትናንቱ የአዲስ አበባን ህዝብ ለማስመታት ዱላ እያቀበለ ነው።

ኢህአዴግ መቼም ኢህአዴግነቱን አይለቅም የትናንቱን ስህተት ዛሬ በመድገም ላይ ነው ያልተረዱት ነገር ትናንት ወያኔን በአፅንኦት ስንቃወመው የነበረውን አካሄድ ዛሬም ኦዴፓ እየደገመው ነውና መቃወማችንን እንደማናቆም ነው።

በመግለጫ ጋጋታ በእስር እንዲሁም በግድያ የህዝብን ጥያቄ ማስቆም አይቻልም እየተነሳ ያለው የህዝብ ጥያቄ ነው ይህን ደግሞ ማንም እንዲሁም ምንም ሊያስቆመው አይችልም።

በትውልድ ከተማዬ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ እስር አይደለም ሞት ቢመጣ በደስታ ነው የምቀበለው ምክንያቱም አዲስ አበባን ለዘረኞች አሳልፈን የሰጠን ዕለት ደረቴን ነፍቼ የማወራለት የኢትዮጵያዊነት ስሜት ኢትዮጵያ ላይ አበቃለት ብዬ ስለማምን ያን ከማይ ደግሞ ሞቴን እመርጣለሁ። – እየሩሳሌም ተስፋው

Share.

About Author

Leave A Reply