የአዲስ አበባ ስታድየም የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያ ተገጠመለት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

አዲስ አበባ ስታድየም በዛሬው ዕለት የአየር ብክለት መለኪያ መሣሪያ እንደተገጠመለት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት መሳሪያውን በይፋ ስራ አስጀምሯል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አትሌት ኃይሌ ፥ ማህበሩ ኢትዮጵያን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለየ መርጦ መሳሪው በኢትዮጵያ እንዲገጠም በማድረጉ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፥ ይህ መሣሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ በአሁኑ ሰዓት በፈረንሳይ – ሞናኮና በአርጀንቲና – ቦነስ አይረስ ብቻ የሚገኝ ነው ብሏል።

እንዲሁም መሳሪያው ለሀገሪቱ የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አብራርቷል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply