የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሄዳል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ዶክተር ታቦር ገብረ መድህን ገለጹ።

አፈ ጉባኤው ዶክተር ታቦር ለኢዜአ እንዳሉት ምክር ቤቱ ነገ ነሃሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም በሚያካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎች መካከል አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን ማጽደቅ አንዱ ነው።

ሌላው ምክር ቤቱ በወረዳ ደረጃ የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀትን የሚመለከት አዋጅም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል አፈ ጉባኤው።

ምክር ቤቱ ሓምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሔደው ጉባኤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተሻሻለው አዋጅ መሰረት አዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ሰጥቶ ነበር።

በወቅቱ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በምክትል ከንቲባነት የከተማዋ ዋና ከንቲባ ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስና ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔን ደግሞ በምክትል ከንቲባነት መሾሙ ይታወሳል።

መዲናዋን ለ6 ዓመታት ገዳማ በከንቲባነት ያገለገሉት ከንቲባ ድሪባ ኩማ አሁን ላይ በአምባሳደርነት ተሹመው ቦታውን መልቀቃቸው አይዘነጋም።

 

Share.

About Author

Leave A Reply