የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ የስምንት ቢሮ ኃላፊዎችና የሰባት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ሾሟል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ የስምንት ቢሮ ኃላፊዎችና የሰባት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን ሾሟል በቅርቡ የትራንስፓርት ሚኒስትር ሆነው በተሾሙት በወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምትክ ኢንጂነር እንዳወቅ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር እና የንግድና እንድስትሪ ቢሮ ኃላፊ ሆኖ ተሹመዋል ።

በተሻለ ሁኔታ ተደራጅተዋል የተባለውና በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ በእጩነት ቀርበው በአብላጫ ድምፅ የሚከተሉት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሹመት ተሰጥተዎል።

1. አቶ ኤፍሬም ግዛው በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

2 . አቶ ታደሰ በንቲ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

አቶ ሞላ ንጉሴ በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የከተማ ልማት ፣ ኮንስትራክሽንና አከባቢ ጥበቃ ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

4 . ወ/ሮ ሂሩት አፅብሃ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

5. አቶ ይስሐቅ ግርማይ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ

6 . ወ/ሮ አረጋሽ ቸኮል በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የንግድና ኢንዲስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

7 . ወ/ሮ ረውዳ ሡልጣን ሁሴን በቢሮ ሃኃላፊ ደረጃ የመንግስት በጀት ፣ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መሆናቸው ታወቀዋል ።

Share.

About Author

Leave A Reply