የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለድምጻዊት ቤቲ ጂ ዕውቅና ሊሰጥ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከከንቲባ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለወጣቷ አርቲስት ቤተልሔም ጌታሁን (ቤቲ ጂ) እውቅና ሊሰጥ ነው፡፡

አርቲስቷ በጋና ዋና ከተማ አክራ በተካሄደው አለም አቀፍ የሙዚቃ ውድድር አሸንፋ የሀገሯን ስም በማስተዋወቅ ከተማ አስተዳደሩ ቅዳሜ ታህሣሥ 27 ቀን 2011 ዓ.ም በጌትፋም ሆቴል የእውቅና ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የኪነ-ጥበብ አፋቃሪያን ይታደማሉ ሲል ከቢሮው የተገኘ ዜና ጠቁሟል።

ቤቲ ጄ ከቅርብ አመታት ወዲህ ዝናዋ ከሀገር አልፎ በአፍሪካ እየናኘ ይገኛል። በተለይም በኮክ ስቱዲዮ በተደጋጋሚ ጊዜ በመቅረብ ከበርካታ የአፍሪካ ዝነኛ ሙዚቀኞች ጋር በርካታ ዝግጅቶችን አቅርባለች።

በቅርቡም አፍሪማ በተሰኘው ውድድር ላይ ተሳትፋ ሶስት ወሳኝ ሽልማቶችን አግኝታለች።

Share.

About Author

Leave A Reply