የአዳማ/ናዝሬት ነዋሪዎች የከተማው አስተዳደር እና በቄሮ ስም የሚንቀሳቀሱ በጥምረት እየፈጠሩት ያለውን የመብት ጥሰት በሰላማዊ ሰልፍ አወገዙ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዳማ/ናዝሬት ነዋሪዎች የከተማው አስተዳደር እና በቄሮ ስም የሚንቀሳቀሱ በጥምረት እየፈጠሩት ያለውን የመብት ጥሰት በሰላማዊ ሰልፍ አወገዙ

በዛሬው እለት ሚያዚያ 14 ቀን 2011 ዓ.ም ከረፋዱ 2 ስዓት ጀምሮ በናዝሬት ከተማ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ነዋሪዎች የመንግስት ታጣቂ የሆኑ የክልሉ ፖሊሶች በቄሮ ስም ያደራጇቸው ወጣቶች ጋር በማበር የግለሰቦችን መኖሪያ ለማስለቀቅ እያደረጉ ያለው ህገ ወጥ እንቅስቃሴን ተከትሎ ቀደም ብሎ ያስነሱትን ግጭት በመቃወም መስተዳድሩ የናዝሬት ከተማ ነዋሪዎችን መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት እንዲያስከብር ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ በከተማው ጠይቀዋል ።

በቄሮ ስም የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ከአስተዳደሩ የጸጥታ ክፍል እና አንዳንድ የቀበሌ አስተዳደር ጋር በመተባበር በከተማው ውስጥ እያደረጉ ባለው ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ግጭት ተፈጥሯል፣ነዋሪዎች ከቤታቸው ለማፈናቀል ተሞክሯል ንብረት ላይ ጉዳት ደርሱዋል የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ ድርጊቱን የከተማው አስተዳደር በአስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቀዋል።

በሰልፉ ፖሊስ ጣልቃ በመግባቱ አንድ ሰው በጥይት ሌላኛው ደግሞ በጩቤ መቁሰሉ የአይን እማኞች የገለጹ ሲሆን የክልሉ ፖሊስ ስለ ግጭቱ የሰጠው መግለጫ የለም።

የህዝቡን ቁጣ የተቀሰቀሰው ሰሞኑን ተደጋግሞ እንደተጠቀሰው አንድ በናዝሬት የሚኖሩ አባት ከ40 ዓመት በላይ ከሚኖሩበት ቤታቸው እንዲወጡ መደረጋቸውን በመቃወም ወጣቶች ተደራጅተው ተቃውሟቸውን በማሰማት ድርጊቱን ለመከላከል ቢሞክሩም ሰሚ በማጣታቸው የዛሬው የሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱን ነዋሪዎቹ ጠቅሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ቀደም በአዋሳ ከተማ የደቡብ ክልልን መቀመጫነት በመቃወም አዋሳ የሲዳማ ነች በሚል በወላይታ ብሄረሰብ አባላት ላይ ወጣቶችና የከተማው አስተዳደር ውስጥ ያሉ ግንባር ፈጥረው ባስነሱት ግጭት በአሰቃቂ ሁኔታ የሰው ሕይወት ጠፍቶ ብዙዎች በከተማው በቤተ ክርስቲያን እስከመጠለል የደረሱበት ግጭት ከተከሰተ በሁዋላ የአዋሳ እያደገ የመጣ የአገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስት መዳረሻነት በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰ ሲሆን የሰሞኑ እንቅስቃሴ ወደ ከፋ ግጭት አምርቶ ናዝሬትም /አንዳማም ላይ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋና ተመሳሳይ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳት እንዳይደርስ ክልሉ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ስራውን ሊሰራ እንደሚገባ የሚገልጹ ወገኖች አሉ።

ህብር ራዲዮ

Share.

About Author

Leave A Reply