የአጼ ቴዎድሮስ የልደት ቀን እና መታሰቢያ ቀን ሊዘከር ነው፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የሀገራቸውን እድገት ለማየት ሌት ተቀን ሲተጉ የነበሩ የክፍለ ዘመኑ ምርጥ መሪ ናቸው፡፡ሀገራቸው ከሁሉም ልቃ ለማየታ ከነበራቸው ራዕይ አንጻር በርካታ ስራዎችን አከናውነዋል፡፡
• የኢትዮጵያን አንድነት ከተከፋፈለ የአገዛዝ ስርዓት ወደ አንድ ማምጣት
• ዘመናዊ ኢትዮጵያን መፍጠር
• በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኢንዱስትሪ ጋፋት ላይ ማቋቋማቸው
• የዘመነ ወታደራዊ አቅም ማደራጀት
• ወታደራዊ ስነ-ልቦና ማለማመድ
• ጠንካራና ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የተውጣጣ ወታደራዊ ስብጥር እንዲኖር ማድረግ
• በደሞዝ የሚተዳደር ወታደር እንዲኖር ማድረጋቸው
• የቤተ ክህነት መርህን ለማደራጀት ያደረጉት ስራ
• የባሪያ ንግድ ማስቆም
ከሚያዝያ 4 ጀምሮ የንጉሱ 2 መቶ አመት የልደት ቀን እና 150ኛ ዓመት መታሰቢያ ቀናቸው በተለያዩ አካባቢዎች ይዘከራል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ እና ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን በተለያዩ አውደጥናቶችና ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብ ኪሚያዝያ 4 ጀምሮ ይዘከራል፡፡
መረጃውን የገለጹልን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ማርሸት ግርማይ ናቸው፡፡

ምንጭ ፦ አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

Share.

About Author

Leave A Reply