የአፍሪካ ዩኒቨርስቲዎች የስፖርት ወድድር ላይ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ሰኔ 24 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ዘጠነኛው የአፍሪካ ዩንቨርስቲዎች የስፖርት ውድድር ዛሬ ተጠናቋል።

በዚህ ወድድር ኡጋንዳ በ16 ወርቅ፣ በ17 ብር እና በ11 ነሃስ በአጠቃላይ በ44 ሜዳሊያዎች አንደኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያ በ13 ወርቅ፣ 20 ብር እና በ22 ነሃስ በአጠቃላይ በ55 ሜዳሊያዎች ሁለተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

በውድድሩ ጋና በ18፣ ደቡብ አፍሪካ በ16፣ ሴኔጋል በ13 እና ቦትስዋና በ11 ሜዳሊያዎች ከሶስት እስከ አምስት ያሉትን ደረጃዎች በተከታታይ በመያዝ ተቀምጠዋል።

ቀጠዩን ደረጃዎች ዚምቡቤ፣ አይቬሪ ኮስት፣ ዛምቢያ፣ ሞሪሸስ፣ ቤኒን፣ ናይጄሪያ፣ ማዳጋስካሪ ፣ጊኒ፣ ታንዛኒያ እና ሴራሊዮን በተለያየ የሜዳሊያ መጠን ከ6 እስከ 16 ያሉት  በመያዝ አጠናቀዋል።

በውድድሩ በወንዶች ጋና አንደኛ ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ በሴቶች ደግሞ ኡጋንዳ ቀዳሚ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች።

በተመሳሳይ ኒዴጄ ዩንቨርስቲ ከተቋማቱ በወንድና በሴት ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል።

በመሆኑም በተቋማት አጠቃላይ የሜዳሊያ ብዛት መሰረት ኒዴጄ፣ አዲስ አበባ እና የልማት ጥናት ዩኒቨርስቲዎች ከአንደኛ እስከ ሶስት ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ አጠናቀዋል።

ለአንድ ሳምንት በመቐለ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የስፓርት ውድድር ሰጠናቀቀ የተለያዩ እንግዶች የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል።

Share.

About Author

Leave A Reply