የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ መጀመሩን የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቀው፥ ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተገመገሙና ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ ድርጅቱ ከመስከረም አጋማሽ በኃላ በሚካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የሚቀርብ ሪፖርት ላይም ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በወቅታዊ ድርጅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply