የኢሳና አፋር ደም አፋሳሹ ግጭት መቼ ነው የሚያበቃው? እንዴስ ያበቃል? – አካደር ኢብራሂም

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በኢትዮጵያ ውስጥ ዝነኛ የሆነ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ፣ ማለቂያ የለለውና መፍትሄ ያልተግኝለት ጦርነት። በተለምዶ በግጦሽና በሳር የሚፈጠር የአርብቶ አደሮች ግጭት በመባል ይታወቃል።

ጉዳዩ ግን ሰፋ ያለ ሌላ ትኩረት የሚስብ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያነገበ ስለመሆኑ ብዙ የተባለ ቢሆንም የተገኘ መፍትሄ ግን የለም። ችግሩ የሚመለከተው አካል መፍትሄ አለመስጠቱ ብቻ አይደለም። ዋናው ችግሩ መንግስታት የሁለቱ ወገኖች ግጭትን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀማቸው ነው።

በዚህ ጉዳይ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ምሁራን ብዙ ጥናቶች አድርገዋል። በጣም ብዙ ጊዜ ደግሞ በሃይማኖት አባቶችና በባህላዊ ሽምግልና ዕርቅ ተሞክሯል። ችግሩ ግን ሊቆም አልቻለም። ለምን ይሆን?
የታሪክ ደርሳናት እንደሚናገሩትና ኢሳዎችም ጭምር የማይክዱት አንድ ሀቅ አለ። የኢሳ ሶማሌ ጎሳ ከዘላዓ ወዲህ የሚታወቁበት መሬት እንዳልነበራቸውና በተለያዩ ጊዜያቶች በተደረጉ ጦርነቶች ግዛታቸውን እያስፋፉ እንደመጡ ይነገራል።

ብዙ ሰዎች በተለይ አሁን አሁን ከማንነትና ከመሬት ይገባኛል ጋር የሚያያዙ ግጭቶች ከፌደራሊዝም ጋር ያያዙታል። የኢሳና አፋር ግጭት ግን በጣም የቆየና ቁርጠኛ የሆነ ገለልተኛ ውሳኔ የሚፈልግ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ከንጉሠ ነገስት ሃይለስላሤ አገዛዝ ዘመን ጀምሮ በኢሳና በአፋር መሃል የተደረጉ ስምምነቶችን ጥሶ የሚገኘው የኢሳ-ሶማሌ ጎሳ እንደሆነ ማስረጃዎች ያሳዩሉ።
የኢሳ (ሶማሌ) ድንበር ከአፍደም ወደ አሁኑ የሶማሌ ክልል 147 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንደነበረ በ1962 ዓ.ም በኤረር ላይ በአፋርና ኢሳ መካከል በተደረገ ስምምነት ተገልጿል። ነገር ግን በአሁኑ ግዜ ኢሳዎች አፋርን እያጠቁ ያሉት ከኤረር 300 ኪ.ሜ. ወደ ውስጥ ገብቶ የአዋሽ ወንዝ ዳርቻ አዳይቱ፣ ኡንዳፎኦ እና ገዳማይቱ በተባሉ

Share.

About Author

Leave A Reply