የኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተጀመሯል፡፡
በኢትዬጵያና በአውሮፓ ህብረት መካከል በኢኮኖሚ ልማት ፤ በማህበራዊ፣ በኢንቨስትመንትና በንግድ ላይ ያተኮረው ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡
መድረኩን የሚመሩት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ባደረጉት ንግግር ምክክሩ በኢትዬጵያና እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚጠቅም ገልጸዋል፡፡
ምክክሩ በኢትዬጵያና እና በአውሮፓ ህብረት መካከል እ.ኤ.አ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈረመው የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት አካል ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት

 

Share.

About Author

Leave A Reply