የኢትዮጵያ ሕዝብ አሰፋፈር እና ስንክሳሩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሃገራችን ኢትዮጵያ ሦስት ዓይነት የሕዝብ አሰፋፈር ሁኗል /ተካሂዷል /ተደርጓል። አንዱ በፍልስት ይህ ተፈጥሯዊ የሰዎች ድርጊት እንቅስቃሴ Natural human phenomenon ነው ከሞላ ጎደል በዚህ መንገድ ነው አሁን ዓለም ላይ ያለው ሕዝብ የሰፈረው የከተመው ምናልባት የሰው መገኛ ከሆነቺው ኢትዮጵያ ይሆናል የሰው ልጅ ፍሰት ሀ-ብሎ የተጀመረው “ምልዕዋ መሬትን እንዳለው” ሰለሆነም ጥንት በነፃ መሬት ባዶ ቦታ ላይ በፍልሰት የሰፈረ የመጣ የከተመ ሕዝብ መሬቱ ቦታው የእሱ የራሱ ነው ባለቤቱም እሱ ነው እዚህ ላይ እንካ ስላንትያ አያስፈልግም።

ሁለተኛው – በሰፋራ ዘመቻ ፕሮግራም, ይህ በደርግ ዘመነ-መንግስት የሆነ ድርጊት ስራ ነው,ሕዝቡን ከሰሜን ኢትዮጵያ በግዳጅ በዘመቻ ወደ ማያውቀው አገር ቦታ ረዥም ርቀት አጓጉዞ አሳፈሮ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ያመጣው ያሰፈረው ነው, ምንም እንኳ ቦታው ባዶ መሬት የነበረ ቢሆንም ባለቤት አለው ልክ እንደ ማንኛውም የብሔር ብሄረሰብ, ጎጃም, ትግራይ መሬት, ይሁን እንጂ ይህን ሕዝብ በጉዳዩ ላይ አሁን ማንም ኢትጵያዊ ተጠያቂ ሊደረገው አይገባም ፈቅዶ ወይም በወረራ በሃይል የመጣ የሰፈር ስላልሆነ ይልቅ የክልሉ መንግስት ነገሩን እንደ ኢትዮጵያዊነቱ ተገንዝቦ እንደ ወገኖቹ አስበዋቸው መልካም ማለፍያ አስትደደር ከእሱ ይጠበቃል።

ሦስተኛው – የምንሊክ ሰፋሪዎች ሰለሚባሉት, ይህ በግዛት ማስፋፋት ወቅት መሬትን በወታደራዊ ወረራ በሃይል, በግፍ በኢ-ፍትሃዊ መንገድ ወዘተ. ሕዝብን ከቀየው ከቦታው በማስለቀቅ በማፈናቀል በማባርር, ወዘተ. መሬት ቦታን የመያዝ ድርጊት ተደርጎ ይወሰዳል በቀጣይም እነኝህ ሕዝቦች ራሳቸውን እና አካባቢያቸውን ለማሻሻል ለማሳደግ ለመቀየር ለመለውጥ ለማሰልጠን ወዘተ ሳይችሉ ሳይበቁ ዕድል ሳያገኙ ለዘመናት በድህነት የበይ ተመልካች ሁነዋል ፅያፍ ስድቦችን ንግግሮችን ትተን አሁን ላይ ሁኖ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሦስት አራት ትውልድ በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ ድርጊት አሁን ላሉት የልጅ ልጅ ልጆቻቸውን ትውልድ ቀጥታ ተጠያቂ ማድረግ በጣም ይከብዳል አሁንም የአንድ ሐገር ሰዎች ነን አንድ ዜጋ ነን አንድ መንግስት ነው ያለን ካሳ ለምጠየቅም አይመችም።

እናማ ይህ ሽምግልና ያሸዋ, ይቅርታና እርቅ ይጠይቃል በአፍሪካ ሕብረት በተባበሩት መንግስታት /ዓለማቀፋዊ እውቅና ባለው መልኩ ሁኔታ ስምምነቱ መስራት መሆን አለበት /recognized and protected conciliation concession/ የጓሮ ስምምነት አለመሆኑ ማስመስከር ይገባል በዚህ በተደረሰበት ይቅርታና – እርቅ ስምምነት እና በተዘጋ ፋይል, በቀጣይ ወደፊት አፍራሽ ይሁን አሰፈራሽ የሚሆን ሰው ወይም ቡድን ከትኛውም ወገን ይሁን ዓለምአቀፍ ወንጀለኛ ተደርጎ ይወሰዳልና እርቁ መካሄድ ያለበት አሁን ባሉት አዲስ ትውልድ ወጣት ሰዎች መሃል እንጂ ትላልቅ ሰዎች ስም ባረጁባፈጁ “ገዥ ፊተውራሪ በነበርኩበት አገር ራሴን ዝቅ አድርጌ ይቅርታ ከምጠይቅ ሽ ሞት ብሞት ይሻለኛል” በሚሉት ከጋሻ-ጃግሬዎቻቸው በቀል አርግዘው አጋጣሚ ቀን-ጊዜ በሚጠብቁ በእባብ አማካሪ ሰዎች መሃል አይደለም መሆን ያለበት እነዚህ ሰዎች ልባቸው በጥላቻ በክፋት በተንኮል በቂም ጥላሽት ጠቁሮ ነጭ ፅዱ ልብስ ለብሰው ቤተ-እምነት /Mosque Church/ ለታይታ የሚመላለሱ ናቸው መጭው ጊዜ ዘመን የአዲሱ
ትውልድ እና የልጆቻቸው የቀጣይ ትውልድ የራሳቸው ነውና።

በባህላችን እውነትን ተናገሮ እመሸበት ማደር እንደምንለው, እንዲሁም ‘ውሽት ለመናገር እትሻም ምላሴ – ለእውነት እሞታለሁ አልሳሳም ለነፍሴ ለሕይወቴ” እንዳለው አርቲስት ዘፋኝ ጥላሁን ገስስ እውነትን ወዶ ፈልጎ አውጥቶ አንስቶ ተናግሮ እርቅን መሻት የአዋቂዎች የልባሞች የሩቅ አሳቢዎች ባህሪ ስነ-ምግባር ስብዕናም ነው ለአፍሪካ ሕብረት አንድነት ውህደት የምትታር የምትተጋ ኢትዮጵያ የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች ሽሙጥ መስማት በዚሁ መሸማቀቅ መፍቀድም የለብንም በብዙ ማሰብ ማስተዋል ያስፈልጋል ተቀጥያ በበጎ አድራጎት የሆነ ለሌላ ሀገር ዜጋ መሬት ቦታ መስጠት ማስፍር ከሙስና /corruption/ በፀዳ አሰራር ይመስለኛል።

ለምሳሌ ለጀማይካን /Jamaican / ራስ-ተፈሪያን ሌላው ኢትዮጵያውያን ሁነው ሰፍረው ቤተሰብ አፍርተው ለዘመናት ኑረው ከቆዩ በኋላ ሀብታም ቤተሰቦቻቸውን አግኘተው ባህር ተሻግረው በመሄድ ላይ ያሉ ቤተ-እስራኤል ካይላ የአፄ ኃ/ስላሴ ተፈሪ መኮነን ጃነሆይ የጠቅላይ ግዛት የክፍለ-ሀገር አስተዳደር ክልል አከላለል አሁን ካለው ከመጣው ለውጥ ጋር የሚሄድ በመሆኑ የደርግና የኢህአደግም ቢሆን እንዲሁ ግድፈት ሰላለው በቀጣይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች እና መንግስት የጋራ አቋም ስምምነት ውሳኔ መሰረት እርማት ማስተካከያ ማሻሻያ ወዘተ ስራ ይስራል ይደረጋል የሚል ከፍተኛ እምነት አለኝ እናማ ሙሉ የኢትዮጵያ መጋጋት ሁኔታ ጊዜ ይፈጠራል ሰላም ይሆናል
የሁላችንም የቀን-ተቀን ፀሎት ነው።
ትዕግስቱን ይሰጠን — አሜን
ይቅርታው እርቁ
ጥር 2011 ዓም

Share.

About Author

Leave A Reply