የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቋራ እና መተማ ጥበቃ እያደረገ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በምዕራብ ጎንደር ዞን ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስነው ደንበር አካባቢ በተከሰተው ግጭት በሰው ህይዎት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ የግጭቱ ምክንያትም የእርሻ መሬት ይገባኛል ጥያቄ መሆኑን ተሰምቷል፡፡

ሱዳንን ከኢትዮጵያ በሚያዋስነው የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ መሬት ላይ ሱዳኖች የይገባኛል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

በግጭቱ ምክንያት በመተማ ደለሎ በኩል የሚገኝ የሱዳን ጦር ተደምስሷል፤ አንድ የሱዳን ሻለቃ አመራር ህይዎቱ አልፏል፡፡ በቋራ ነብስ ገበያ በኩል በተፈጠረው ግጭት ደግሞ 7 የሱዳን ወታደሮች ሞተዋል፤ 2 መኪና እና 7 የጦር መሳሪያዎችም ተማርከዋል፡፡

ሶስት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እና ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህይዎታቸዉ ማለፉ ተሰምቷል፤ 6 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዉ ሆስፒታል መግባታቸው ታዉቋል፡፡ ከነዚህ መካከል ሁለቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸዉ፡፡

ምንጭ: – አብመድ

 

Share.

About Author

Leave A Reply