የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የጋራ ኮሚቴ መግለጫ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኮሚቴዉ መሪዎች መግለጫ፤ የመክፈቻዉ ንግግር፤ ዱዓ-ሐዲሱም የሠላምን አስፈላጊነት፤ በአንድነት የመቆምን ጠቃሚነትን አፅንኦት የሰጠ ነበር።ለምን? ኢትዮጵያዉያን በጣሙን ሙስሊሞች የሠላም ሥጋት፤የአንድነት ችግር አለባቸዉ ይሆን?

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ እስከ መጪዉ ታሕሳስ አጋማሽ ድረስ ሥራዉን እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ።የኮሚቴዉ መሪዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ኮሚቴዉ ያዋቀራቸዉ አራት ንዑሳን ኮሚቴዎች፤ ጥናት እና ሥራቸዉን ከሞላ ጎደል አጠናቅቀዋል።በየንዑሳን ኮሚቴዎቹ የተደረጉ ጥናቶች እና ሥራዎች ላይ ዉይይቶች ተደርጎባቸዉ አዳዲስ ሐሳቦች ተካትቶባቸዋል።በመግለጫዉ መሠረት በጥናቶች፤ በተሰበሰቡ አስተያቶች እና በተከናዎኑ ተግባራት ላይ በተመረጡ ከተሞች ተጨማሪ ዉይይት ተደርጎ የመጨረሻዉ ዉጤት ትሕሳስ 15 ይጠናቀቃል።

የኮሚቴዉ መሪዎች መግለጫ፤ የመክፈቻዉ ንግግር፤ ዱዓ-ሐዲሱም የሠላምን አስፈላጊነት፤ በአንድነት የመቆምን ጠቃሚነትን አፅንኦት የሰጠ ነበር።ለምን? ኢትዮጵያዉያን በጣሙን ሙስሊሞች የሠላም ሥጋት፤የአንድነት ችግር አለባቸዉ ይሆን? ጠየቅሁ? «እንዴታ!» መለሱ የኮሚቴዉ ሊቀመንበር ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ጥያቄዉን በጥያቄ፤ ሙሉ ሰላም እና አንድነት ቢኖርማ «የጋራ ኮሚቴ ለምን አስፈለገ?»

ኮሚቴዉ ታሕሳስ አጋማሽ ያጠናቅቀዋል የተባለዉ ሥራ እና ዉጤቱ አሁንም አልጠፋም የሚባለዉን ልዩነት፣ ሲሆን ያስወግዳል ካልሆነም ያዳክመል ነዉ-ተስፋ እምነቱ።ኮሚቴዉ ሥራዉን አጠናቀቀ ማለት ግን፤ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንደሚሉት፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ጉባኤ አዳዲስ መሪዎች ተመረጡለት ማለት አይደለም።

ኮሚቴዉ ካለፈዉ ነሐሴ መጀመሪያ ጀምሮ ያከናወናቸዉን ተግባራት ባቀረበበት ዘገባዉ ሥራዉን ቶሎ እንዲያጠናቅቅ ከሚደረጉ ግፊቶች፤ የኮሚቴዉ አባላትን ካንዱ ወይም ከሌላዉ ቡድን ጋር እስከመፈረጅ፤ ከአስተዳደራዊ ጥያቄ፤ በሥፍራዉ የተነሱ ቀዉሶችን እንዲያስወግድ እስከ መጎትጎት የደረሱ ችግሮች፤ ፈተና እና እንቅፋቶች እንደገጠሙት አስታዉቋል።በችግር ፈተናዉ መሐል ግን ከተሰጠዉ ኃላፊነት ዉጪም ቀዉሶችን ለማርገብ ብዙ ጥሯል።ከተለያዩ የዉጪ ተቋማት ልምድ ቀስሟልም-እንደዘገባዉ።

DW

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋዓለም

Share.

About Author

Leave A Reply