“የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ምድራዊ ሶኦል ናቸው!” አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በሀገራችን በ2001 ዓ.ም በተግባር ስራ ላይ የዋለው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ፣ በቀዳሚነት ተፈፃሚ ከሆነባቸው ኢትዮጵያውያን መካከል (ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት ዓለሙና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ይገኙበታል) አንዱ ነበር። በአዋጁ ተጠርጥሮ የታሰረው ህዳር 12 ቀን 2002 ዓ.ም ሲሆን ላላፋት 7 ዓመት ገደማ በግፍ እስር ታስሮ ተሰቃይቷል። ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለሁለት ቀናት ያህል ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ ተገረፏል። የእጅ አጥንቱ ተሰብሯል። ከቃሊቲ እስከ ዝዋይ የግዞት እስር ጨለማ ቤቶች በተደጋጋሚ ቅጣት ታስሯል። በህክምና እጦትና ክልከላም ተሰቃይቷል። የቅጣት ቅጣቶችን በተግባር አይቷል። …በቅርቡ ከእስር ከተፈቱት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ነው – ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ፓለቲከኛው አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር።

ከአቶ ዘሪሁን ጋር ዛሬ ከሰዓት በኋላ፤ በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝቼ ረዥም ሰዓታት ስለግፍ እስራቸው፣ ስቃያቸው፣ የእስር ቤት ቆይታ፣ ስለሀገር ሁኔታ …ተጨዋወትን። …ካሳለፈው መከራ ከመከራው በላይ ቆሞ፣ ፈገግ እያለ ሀሳቡን ይሰነዝራል። አንዳንዴም ይስቃል። …መከራን በመናቅ ልበለው? …መከራን መናቅ ታላቅ አቅም ይጠይቃልና!

….ዛሬ ከአቶ ዘሪሁን ጋር የነበረኝን ቆይታ ደስ የሚል ነበር። በሌላ ቀን እመለስበታለሁ። ብዙ የማላውቃቸውን ጉዳዮችንም ከአቶ ዘሪሁን ተምሬያለሁ።

…በመጨረሻም፣ “ስለ ኢትዮጵያዊ እስር ቤቶች ሁኔታ ምን ብዬ ልንገርህ? …’ምድራዊ ሲኦል’ የሚለው ቃል ይገልፃቸዋል። ከዚያ መከራ እንድንወጣ የብዙ ወገኖቻችን ደም ተገብሯል። የደም ዋጋ ነው የተፋታነው። አካል ጎድሏል። ከሀገር ውስጥ እስከውጪ ሀገራት ድረስ ያሉ ዜጎቻችን ድምጻቸውን አሰምተውልናል። ዓለም አቀፍ ተቋማትም ጭምር። ለዚህ አመሰግናለሁ። ለፈጣሪም ትልቅ ምስጋናዬን አደርሳለሁ። በነገዋ ኢትዮጵያዊ ተስፋ ይታየኛል። ሀገራችን ዴሞክራሲ፣ ነጻነት፣ ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት እንድትሆንም እሻለሁ። እኔም በመንገዴ መታገሌን እቀጥላለሁ።” የሚል ሀሳብ ሰንዝሯል – አቶ ዘሪሁን።

(በኤሊያስ ገብሩ የቀረበ)

 

Share.

About Author

Leave A Reply