የኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የዶላር ክምችቱ የሦስት ወራት የሀገሪቱን የገቢ ንግድ ለማከናወን እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የመጠባበቂያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህም የሦስት ወራት የሀገሪቱን የገቢ ንግድ ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፡፡

ማክሮ ኢኮኖሚው በመዛባቱ ምክንያት ቀውስ ውስጥ ሊከት የሚችል ደረጃ ተደርሶ ነበር፤ አሁን ግን የተለዩትን ችግሮች ማስተካከል በመቻሉ ከችግሩ እተየወጣ ነው ብለዋል ዶክተር እዮብ።

ይህም ለመጠባበቂያ ገንዘቡ መገኘት ምክንያት እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡
የሀገር ውስጥ ምርታማነትን በመጨመር የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ማሳደግ ካልተቻለ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የሚያመጣቸው ችግሮች ፈታኝ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ችግሩን ለማስተካከል ለግሉ ሴክተር ተሳትፎ ልዩ ትኩረት መሰጠቱንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply