የኢትዮ ቴሌኮም ለኢንተርኔት አቅራቢነት ለግል ድርጂት ፈቃድ ሰጠሁ ማለቱ ጥያቄ አስነሳ።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ኢትዮ ቴሌኮም ጂቱጂ (G2G) ለተባለ አገር በቀል ኩባንያ የኢንተርኔት አቅራቢነት ፈቃድ መስጠቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ሆኖም ጉዳዩ  በአንዳንዶች ዘንግ ጥያቄ አስነስቷል።

ብዙዎች ድርጊቱን የመንግስትን ገንዘብ ወደ ግል ኪስ ለማዘዋወር የተደረገ መላ ነው ሲሉ ተቃውመውታል።

ኩባንያው በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሰርቨር ስር በመጠቀም ለተቋማት፣ መኖሪያ ቤቶች እና ለግለሰቦች ኢንተርኔት እንዲያቀርብ ስምምነት ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ የግል የተባለው ድርጂት በተለይም የህወሀት ሰዎች የሆኑ ባለ ስልጣናት ያቋቋሙት መሆኑን እና ይህም ሆን ተብሎ የተደረገ ሴራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጀዋር መሀመድ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንደተነተነው ይህ ፕሮጄክት አስቀድሞ የተጠናና ከዚህ ቀደም የዶክተር ደብረ ጽዮን ኢሜይሎች በሀከሮች በተበረበኡ ጊዜ ይፋ መደረጉን አስታውሷል።

በወቅቱም የኢትዮ ቴሌኮምን ሰርቨር በመጠቀም አገልግሎት የሚሰጥ የግል ኩባኒያ ለማቋቋም በህወሀት በኩል እየተሰራበት መሆኑን ለህዝብ ይፋ ማድረጉን ጠቅሷል።

Share.

About Author

Leave A Reply