የኢትዮ ኤርትራን ግንኙነት ማጠናከርን ዓላማው ያደረገ ታላቅ ሩጫ በመቀሌ ከተማ ሊካሄድ ነው

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ የሁለቱን ሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር የታላቁ ሩጫ ውድድር በመቀሌ ከተማ ሊካሔድ ነው።

ሩጫውን የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከኤርትራ አትሌቲክስ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት የሚያዘጋጁት መሆኑም ተመልክቷል።

የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኪዳነ ተክለሃይማኖት ለኢዜአ በላኩት ደብዳቤ እንዳስታወቁት ሩጫው የፊታችን ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ይካሄዳል።

አምስት ኪሎ ሜትር ይሸፍናል በተባለው በዚህ ሩጫ ታዋቂ አትሌቶችን ጨምሮ ሁለቱን ሃገራት የሚወክሉ በርካታ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጿል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ ውድድር በአገራቱ መካከል የተጀመረውን ሰላምና ፍቅር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አያይዘው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Share.

About Author

Leave A Reply