የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግብፅ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ጀምረዋል።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኡጋንዳ ሲያደርጉት የነበረውን ቅዳሜ ምሽት በማጠናቀቅ ነው ካይሮ ያቀኑት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግብፅ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት የሚያደርጉ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግብፅ በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤልሲሱ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ አንደሚወያዩም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ካይሮ ከማቅናታቸው በፊት በኡጋንዳ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በቆይታቸውም ከኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ የሁለቱን ሀገራት የንግድና ፖለቲካ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ኡጋንዳ መልካም ስራ ለሰሩ አፍሪካውያን የምታበረክተውን ሜዳሊያ በፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ተበርክቶላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቀደም ሲል በጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ኬንያ ፣ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

Share.

About Author

Leave A Reply