የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኤርትራ አቀኑ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነትን ያድሳል የተባለለትን ታሪካዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

የሀገሪቱ መዲና አስመራም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰንደቅ ዓላማ የደመቀች ሲሆን፥ ወዳጅነትን የሚያጠናክሩ የተለያዩ መልዕክቶችም ተሰቅለውባታል።

ሁለቱ ሀገራት ያካሄዱትን የድንበር ግጭት ተከትሎ ግንኙነታቸውን ለሁለት አስርት ዓመታት አቋርጠው ቆይተዋል።

በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማደስ የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ውሳኔ ማሳለፉ ለግንኙነታቸው ተስፋ ፈንጥቋል።

ኤርትራም የኢትዮጵያን የሰላም ጥሪ በመቀበል በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የሚመራ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ መላኳ አይዘነጋም።

በዚህም ወቅት ለሀገራቱ ግንኙነት መታደስ መንገድ የሚጠርግ ውይይት መካሄዱን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።

Share.

About Author

Leave A Reply