የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂንና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ አማራ ክልል ዛሬ አማራ ክልል ይገባሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂንና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ አማራ ክልል ዛሬ አማራ ክልል እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ሁለቱ መረዎች ወደ አማራ ክልል የሚያቀኑት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አማራ ክልልን እንዲጎብኙ በይፋ መጋበዛቸውን ተከትሎ ነው።

ግብዣውም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ እየፈጠረ የሚገኘው የለውጥ እንቅስቃሴና የኢኮኖሚ ትብብርን ለማመቻቸት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የሚያካሂዱት እንቅስቃሴ አካል ነው።

በመስከረም 2011 በኤርትራ አስመራ የተካሄደው የሶስትዮሽ ምክክር ተከታይ የሆነው ይህ ጉብኝትም ውይይቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ ሲሆን በጎንደርና ባህር ዳር የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎችን መጎብኘትን እንደሚያካትት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውወቋል።

Share.

About Author

Leave A Reply