የእናት ኢትዮጵያ ልጆች የተወጉበት ቀን! ሰኔ 1 ቀን 97 ዓ.ም

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ይህችን ቀን ሳንዘክራት ልናልፍ አንችልም። 13 ዓመት ረዥም ጊዜም አይደለም። ደግሞም የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም ይባላል። እና ይህች ቀን የእናት ኢትዮጵያ ልጆች የተወጉበት ቀን ነው።

የዛሬ 13 ዓመት ሀዳር በምትባል ጋዜጣ ላይ ከፍተኛ አዘጋጅ ሆኜ እሠራ ነበር። ልክ በዛሬዋ ዕለት በመዲናችን ወጣቶች፣ አዛውንቶችና ሌላ ቀርቶ ቦርቀው ባልጠገቡ ህፃናት ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያ ዘግቤዋለሁ።

ከሰኔ 1 ቀን በሁዋላ በነበሩት ተከታታይ ቀናት የሥራ ባልደረባዬ ከነበረው ጋዜጠኛ ፈለቀ ጥበቡ አብርሃም ጋር በመሆን በየተጎጂዎቹ ቤት እየዞርን ስለሁኔታው መረጃ እናጠናቅር ነበር። ሟቾቹ በአብዛኛው የተገደሉት ከሥራ ሲመለሱ፣ ወደቤተ እምነታቸው ሲሄዱና መሰል ማሕበራዊ ጉዳዮቻቸውን ሲያከናውኑ ነበር።

እኒያ በገፍ እና በግፍ የተገደሉ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች ዛሬ 13 ዓመት ሞላቸው። እግዚአብሔር በመንግስቱ ያስብልን። ቤተሰቦቻቸውን በቅዱስ መንፈሱ ያበርታልን። በኢትዮጵያችን ሰማይ ስር ይህ ሰቆቃ በፍፁም አይደገም።

(ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ)

Share.

About Author

Leave A Reply