የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

በዛሬው እለት የተጀመረው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በ9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በሚቀርቡ ትልልቅ አጀንዳዎች ላይ እየመከረ መሆኑን የኦህዴድ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ማካሄድ በጀመረው ስብሰባው 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባዔ ስኬታማ እንዲሆን እየተሰሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲሁም በድርጅታዊ ጉባዔው ላይ የሚቀርበውን ረቂቅ ሪፖርት እንደሚገመግም ይጠበቃል።

በተጨማሪም ማዕከላዊ ኮሚቴው የድርጅቱ የ2011 በጀት ያፀድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫም ያስቀምጣል ተብሏል።

በተጨማሪም ድርጅቱ ከደረሰበት የትግል ደረጃ ጋር ተያይዞ በሚደረጉ ለውጦች ላይ የውሳኔ ሀሳብ ያሳልፋል ተብሏል።

እንዲሁም በሚቀርቡ ረቂቅ ማሻሻያዎች ላይ በመወያየትም ረቂቁን ለማዳበር እና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸው ላይም አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሙለታ መንገሻ

Share.

About Author

Leave A Reply