የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዲጂታል የመንጃ ፈቃድ የመታወቂያ አገልገሎት መስጠት ጀመረ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ የሚስተዋለውን ክፍተት ለመፍታት ዲጂታል የመታወቂያ አገልገሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ምህረት ሻንቆ እንደገለጹት፥ በደቂቃ ሁለት መታወቂያን ማተም የሚችሉ 14 ማተሚያዎችን መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ ማተሚያዎቹ በሰባት የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ማዕከላት የተሰራጩ ሲሆን፥ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ዲጂታል የመንጃ ፈቃድ መታወቂያ ካርዶችን ማስመጣታቸውን ገልጸዋል።

አዲስ መንጃ ፈቃድ ለሚያወጡ ሰዎችም ከማሰልጠኛ ተቋማት መታወቂያ የሚያሰጣቸውን ፈቃድ በገኙ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚያስረክብም አስታውቋል።

መታወቂያውን የትራፊክ ፖሊሶች በቀላሉ ትክክለኛ መሆኑን እንዲለዩ የሚያስችሉ ቁጥራቸው ከሶስት ሺህ በላይ የሆኑ ሶስት የተለያዩ መለያ መሳሪያዎች የሚገኙ ሲሆን በቅርቡ ስልጠና በመስጠት እንደሚሰራጩም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ለዲጂታል መታወቂያው ከ46 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገም ነው የተገለጸው። ዲጂታል የመንጃ ፈቃድ መታወቂያው ሃሰተኛ ወይም ህገወጥ መታወቂያዎችን በብዛት ይዘው የሚያሽከረክሩ ወንጀለኞችን ለመቀነስ እንደሚረዳም ተገልጿል።

በክልሉ እውቅና ከተሰጣቸው ማሰልጠኛ ተቋማት ጋርም በመታወቂያ አሰጣጡ እና አግባብነቱ ዙሪያ ምክክር ተደርጓል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ባለስልጣኑ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማዘመን ከ8 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ መሳሪያዎችን በመግዛት አገልግሎት መጀመሩን ገልጿል፡፡

በዚህም ባለጉዳዮች ጉዳይ ለማስፈጸም ቦታው ድረስ መሄድ ሳይጠበቅባቸው በቀጥታ (ኦንላይን) አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በጸጋዬ ንጉስ

Share.

About Author

Leave A Reply