የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በሜኖሶታ የኢትዮጵያ ቆንፅላ ጽ/ቤትን መርቀው መክፈታቸው ተቃውሞ አስነሳ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(የግል አስተያየት)

የውጭ ገዳይ ሚኒስቴር ስራ ለኦሮሚያ ክልል ከተሰጠ ቆይቷል።

የሜኖሶታ ቆንጽላ ጽ/ቤት ሀላፊ ተደርጎ የተሾመው የኦህዴዱ (ኦነግ ክንፍ) እውነቱ ብላታ ወደ ቦታው ሲያቀና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በአቀባበሉ እንዳይገኙ በመደረጉ ከሳምንታት በፊት በውጩ ነዋሪ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ በክልሉ ፕሬዝዳንት ሲከፈት ኦህዴድ ለኢትዮጵያውያን “ምንም አታማጡም” የሚል ግልፅ መልዕክት እያስተላለፈ መሆኑ ነው።

እነ ዶ/ር አብይ አሜሪካ ባቀኑበት ወቅት ሜኖሶታ ላይ በተፈፀመ ፀያፍ ድርጊት ዶ/ር አብይ የአማራን ህዝብ በይፋ ይቅርታ መጠየቁም ይታወሳል።

በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተመርቆ ዛሬ ሥራ ጀመረ:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ይገኛሉ ተብሎ ቀደም ሲል ተነግሮ የነበረ ቢሆንም በመጨሻው ሰዓት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታዋ አምባሳደር ብርቱካን አያኖና የአሜሪካ መንግግስት ባለስልጣናት በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል::

አቶ ለማ መገርሳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው፣ ምክንያቱ ዐቢይ በአደባባይ “መሪዬ ነው” ብሎናል። አቶ ለማ መገርሳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ነው፣ የክልል አስተዳደር ነው ተብሎ ኤምባሲ መርቆ ይከፍታል። ኦህዴድ ስልጣን ከያዘ በኋላ አቶ ለማ ከዐቢይ ጎን አይጠፋም። ጅቢቲም ዐረብ ሀገራትም ላይ በነበረው ጉብኝት በሙሉ የኦህዴድ ሰዎች ብቻ የልዑክ ቡድን አባል ነበሩ።

አዲስ አበባ ውስጥም ዲፕሎማቶቹን የሚያገኙት ኦህዴዶች ብቻ እየሆኑ ነው! በውጭ ሀገርም ኢምባሲዎችን እየተዟዟረ የሚከፍተው ኦህዴዶች ናቸው። እነ ለማ የአዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን የኤምባሲዎች ስብጥር በአጭር ጊዜ በራሳቸው ሰው ቀይረውታል። ሕወሓር ኮትኩቶ ያሳደገው ኦህዴድ የተለየ መንገድ አላመጣልንም። ሕወሓትን ገፍትሮ በድሮው ጎዳና እየተጓዘ ነው።

(አያሌው መንበር)

Share.

About Author

Leave A Reply