የወልቃይት ነዋሪዎች ካርታውን እንደማይቀበሉት አቤቱታቸውን ለመንግስት ማቅረብ የጀመሩት መቼ ነው?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የወልቃይት ጉዳይ የወያኔ ሽግግር መንግስት ግንቦት  15 ቀን 1985 ዓ.ስለ ሀገሪቱ የፖለቲካ ካርታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነፈሰበት ቀን አንስቶ  እስካሁን ድረስ በግልፅ  በተቃውሞ ውስጥ ይገኛል፡፡  የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ካርታውን እንዳማይቀበለው በወቅቱ በነበሩ የህትመት ውጤቶች በግልፅ ተቃውሟል፡፡ 

ለምሳሌ ያህል፡-

  1. ሙዳይ መፅሔት 1985 ” የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አዲሱን ካርታ አልተቀበለውም”
  2. ጦቢያ መፅሔት ቅፅ 2 ቁጥር 2 1996 ” መልስ ያጣ የወልቃይትና ጠገዴ ህዝብ ዕንባ”
  3. ጉግሳ መፅሔት ቅፅ 4 ሐምሌ 1994 “ማርያም የሁመራይቱ ወይ ፍረጅ ወይ ውረጅ”
  4. ሐዋርያ ጋዜጣ “ወልቃይት” መጋቢት 6 ቀን 1993,
  5. ሐዋርያ ጋዜጣ “የወልቃይት ጠገዴን ጀግና ህዝብ ያስጠቃ ማነው” ጥቅምት 22 ቀን 1995

ይህ ከታች በምስሉ ያለው ደብዳቤ ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ አባቶች ለወቅቱ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ለአቶ መለስ ዜናዊ ድርጊቱን በቃወም ህዳር 11 ቀን 1984 ዓ.የፃፉት ደብዳቤ ነው፡፡

የወልቃይት ጉዳይ በአሁኑ የብአዴን ስብሳባ በአጀንዳነት አለመቅረቡን እየሰማን ነው፡፡ 

Share.

About Author

Leave A Reply