Thursday, January 17

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ16 ዓመት በፊት የወጣውን የውጭ ግንኙነት ሀገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንደሚሻሻል አስታወቀ፡፡

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የውጭ ግንኙነት ሀገራዊ ደህንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ከ16 ዓመታት በፊት ሲወጣ እንደ አይ. ኤስ እና አልሸባብ ያሉ አሸባሪ ቡድኖች ስጋት፣ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ የጤና እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮችን አካቶ እንዲይዝ አልተደረገም፡፡ በመሆኑም ከዓለም ነባራዊና ከኢትዮጵያ የውስጥ ሁኔታ ጋር የሚመጥን ፍተሻ ይካሄዳል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የተገበረው የመዋቅር ማሻሻያ ፖሊሲና ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግና ለማስፈጸም ያግዛል ያሉት አቶ መለስ፣ የሰው ኃይል ምደባውም ሥራና ሠራተኛን ማገናኘት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

እንደ አቶ መለስ ማብራሪያ፤ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተካሄደው ሪፎርም የሰው ኃይል ምደባና ስምሪት፣ የአደረጃጀት መዋቅር፣ የመሰረተ ልማትና የአቅም ጉዳይን መሰረት አድርጎ የተከናወነ ሲሆን፣ ከፖለቲካ አመለካከት የፀዳ፣ የመፈፀም አቅምን ማዕከል ባደረገ መልኩ ነው የተከናወ ነው፡፡ የዚህ ተግባር ዋና ተልዕኮም ዋና መሥሪያ ቤቱንና ሚሲዮኖችም በማጠናከር የዲፕሎማሲ አቅም መገንባት ሲሆን፣ የዚህ ዘመን ትውልድ ዲፕሎማ ቶችን ለመፍጠርም ታሳቢ ተደርጓል፡፡

በሥራ ላይ የዋለው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የማሻሻያ መዋቅር ቋሚ ተጠሪ የሚል አዲስ አደረጃጀት እንዳለውና ቋሚ ተጠሪው የተቋሙን የዕለት ተዕለት ሥራ የሚመራ፣ የሚያስተባብርና ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን አቶ መለስ ገልጸው፣ የ31 ከፍተኛ አመራሮች ምደባ መካሄዱንም አመልክተዋል፡፡ የሚኒስቴሩ የቃልአቀባይ ፅህፈት ቤትም በተሻለ መልኩ እንደሚ ደራጅም አስታውቀዋል፡፡

የተሻለ የሰው ኃይል ከመፍጠር ጎን ለጎንም የመሰረተ ልማት ግንባታ ሥራዎ ችንም የማጠናከር ተግባር በመከናወን ላይ መሆኑን የጠቆሙት ቃል አቀባዩ፣ በሥልጠና ሁለተናዊ አቅም ለመገንባትም ሥራዎች እንደሚሠሩና መገናኛ ብዙኃንም በዲፕ ሎማሲ ሥራ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲ ኖራቸው በሥልጠናው እንደሚካተቱ አመል ክተዋል፡፡

ከህዳር 2011ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄደው 11ኛው የአፍሪካ ልዩ ስብሰባ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚመራው አዘጋጅ ኮሚቴ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አቶ መለስ ተናግረዋል፡፡ ስብሰባው በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

ስብሰባው ከህዳር 5እና6ቀን 2011ዓ.ም በሚኒስትሮች እንደሚጀመርና ህዳር 8እና9 ቀን ደግሞ የመሪዎች ጉባኤ እንደሚካሄድ አመልክ ተዋል፡፡

የስብሰባው አጀንዳም የአፍሪካ ህብረት በጀመረው ሪፎርም ላይ እንደሚያተኩር አስታውቀዋል፡፡ በስብሰባው ላይ 45 የሀገር መሪዎች እንደሚሳተፉና አብዛኞቹም እንደሚሳተፉ ማሳወቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ኢፕድ

Share.

About Author

Leave A Reply