የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚኒስቴር አዳዲስ ሚኒስትሮች ተሹመዋል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የአዳዲስ ሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲሾሙ፤

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ደግሞ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር ሆነዋል፤

የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ደግሞ ወደ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት ተዛውረዋል።

ምክር ቤቱ ሹመቱን በአንድ ተቃውሞ፣ በአምስት ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል። የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ወይዘሮ አይሻ መሃመድ የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን  ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል

Share.

About Author

Leave A Reply