የዛሬው የም/ወለጋ የአምስት ሰዎች ግድያ ሚስጥር

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

”አንድ ወዳጄ ኮንትራክተር ነው። ከስራዎቹ ውስጥ የተለያዩ አስቸጋሪ የድሪሊንግ ስራዎችንም እየወሰደ ይሰራል።

ከጥቂት ወራት በፊት ከወለጋ ነጆ ለአካባቢው ለሚሰራ አንድ ፕሮጀክት ማሽኖቹን አስገብቶ “የአካባቢው አለቆች ነን” በሚሉ ወጣቶች በማሽኖችና በተወሰኑ ሰራተኞች ላይ ጉዳት ደርሶ በሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት በህይወት ተርፈው የሳይቱን ስራ አቋርጠው ወደ አ/አ ተመልሰዋል።

ታዲያ የስራው መቋረጥ ያሳሰባቸው አካላት ይህን ወዳጄን አግባብተው አካባቢው ላይ ምንም ችግር እንደማይደርስ ነግረውና አሳምነው አሁን በቅርብ ስራ ይጀመራል።

ዛሬ በጠዋት ከዚ ወዳጄ የደረሰኝ ስልክ ግን ሰቅጣጭ ዜና ነበረው። እንደነገረኝ የእሱን 5 ሰራተኞች 2 የውጪ ዜጎች(ጃፓንና ህንድ) አንድ ጂኦሎጂስት እና ሁለት ሌሎች ሰራተኞችን ዛሬ ጠዋት በአካባቢው የታጠቀው ሀይል መኪናቸውን አስቁሞ በጥይት ገሏቸው ከነመኪናው እያቃጠላቸው መሆኑን ነገረኝ። እጅግ አሳዛኝ ነው!!!.

እነሱን በሌላ መኪና ይከተሉ የነበሩ ባልደረቦቻቸው ጏደኞቻቸው ከነመኪናቸው ሲቃጠሉ እያዩ ጉድጏድ ውስጥ ተደብቀው ድረሱልን እያሉ ነው አለኝ።
የሰው ህይወት በየቀኑ ያለአግባቡ ይቀጠፋል። የውስጥ ጣጣችንም ከኛ አልፎ ለሌሎች ተርፏል።

ከዚህ አልፎ ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ኢንቨስትመንትንና ንግድን ፖለቲካን የአለምን ሁኔታ …የመሳሰሉትን የምንረዳበት መንገድ አይገባኝም።
መሬትን እንደ መጨረሻ ሀብት እየቆጠርን በሀገሪቷ በመከራ የገባው ባለሀብት ሁሉ ሀገሪቱን ጥሎ ወጥቶ ባዶ መሬት ታቅፈን መቅረታችን አይቀሬ ነው። ያልለማ ሜዳ ተቀቅሎ አይበላም። የክልሉ መንግስትም ይህን እንኳን በአግባቡ ሳይቆጣጠር/ሳይሰራ ህግ አስከብራለው እያለ ሌላው ላይ ይንጠለጠላል። ምእራብ ኦሮሚያ ላይ ያለው ውጥረት ግልፅ የፖለቲካ መፍትሄ ይፈልጋል። መንገዱ ሁላ ተወጥሮ በመኪና አቋርጦ ለሚያልፈው እንኳን አስፈሪ ነው።

በፍጥነት መንቃት አለብን። አለም እኛን የሚያባብልበት ምንም ምክንያት የለውም። ወርውረው ነው የሚጥሉን። ከየትም አለም ስንት አማራጭ እያለው ሊሞት ኢትዮጵያ የሚመጣ ባለሀብት አይኖርም። ”

ቴዲ ጌታቸው ከተባለ ጸሃፊ የወሰድነው መረጃ ነው
ነፍስ ይማር ለሟቾቹ

Share.

About Author

Leave A Reply