የየመን ሀገር ህዝቦች በረሀብ ሊያልቁ ጫፍ ደርሰዋል!

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የእርስ በእርስ ጦርነት ህዝቦቿን እና ህንፃዎቿን የጨረሰባት የመን የተረፉት ህዝቦች እጅግ በአስከፊ የተላላፊ በሽታና ረሀብ የማለቅ አደጋ አንዣብቦባታል።
የፀደይ ወራት አብዮት የሚባለው የምስራቁ ዓለም አብዮት መጠንሸሻው የመን ሲሆን ሶሪያ እና ሊቢያ ግብፅን ያካለለ ሲሆን ግብፅ የአሜሪካ ድጋፍ ስላላት መሪዋን ሆስኒ ሙባረክን አውርዳ ኢታማዦሩን ሹማ ቢጠናቀቅም ቅሉ ብልፅግና ውስጥ የነበሩት ሶርያ የመን ሊቢያ ፈራርሰው የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆነው ህዝቦቿ አልቀዋል ገሚሱ ተሰዷል።
በተለይ ሶሪያና የመን የዚህ ሰለባ ሆና ሀገራቸው ፈራርሰው የሀያላን ጡንጫ መፈታተሻ ሆነዋል!
በተለይም በሀገሪቷ የሚላስ የሚቀመስ እንደሌለ ነው ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ያሉት።

ለእዚህ ዋናው ተጠያቂ ሳውዲ አረቢያ ነች።
ወጣቱ አልጋ ወራሽ የሳውዲን ስልጣን ከተቆናጠጡ ወዲህ አምባገነናዊ ሁኔታ እየታየባቸው እንዳለ ግልፅ ነው።

በተለይም የመንን ከምስራቁ የአረብ ምድር ካርታ ለመሰረዝና የመን የምትባል ከተማና ህዝብ ነበሩ የሚል ታሪክ ለማፃፍ ሳውዲ በትጋት እየሰራች ትገኛለች።
ሳውዲ በአሁን ወቅት ሥልጣኑን በተቆናጠጠው ወጣቱ መሪዋ በምትቀበለው ትዕዛዝ እንኳንስ ለሌላ ዜጋ ይቅርና ለራሷም ዜጋ የማትመለስ ሰው በላ ሀገር ከሆነች ሰነባብታለች ለዚህም ማሳያው በራሷ ዜጋ ጋዜጠኛ ዠማል የደረሰው አሰቃቂ ግድያ እና ቱጃሮቿን በእስር ቤት እንዲማቅቁ የምታደርገው ድርጊቶች ነው።

የአድማስ ጋዜጠኛው ቴዎድሮስ ስለየመን አስከፊው ረሀብ እንዲህ ዘግቦታል፦በዓለማችን እጅግ የከፋ የሚባል ረሃብ በየመን ተከስቷል። የየመን ህዝብ ከግማሽ በላይ በረሃብ የማለቅ አፋፍ ላይ ነው። ሊሞቱ የሚያጣጥሩ ህጻናትን ፎቶ እዚህ ለጥፌ ማሳቀቅ አልፈልም። ግን እንደ ሰው ፣ የየመንን ችግር ዓይቶ ዝም ማለት አይቻልም። አዎ ችግር ሁሉም ቦታ አለ – ሆኖም የየመንን ያህል የአንድ አገር ህዝብ በረሃብ ሊያልቅ ቋፍ ላይ የደረሰበት አገር የለም።

የመን አነሰም በዛ ፣ በርካታ ስደተኛዎቻችንን፣ የቀድሞ የባህር ሃይል አባላቶቻችንን፣ ወደ ሳውዲ ለመሻገር የቻሉ ወገኖቻችንን በደህናው ቀን ያስተናገደች አገር ናት። ገንዘብ ኖሮን ባንሰጣት ፣ ጸሎት ማዋጣት አያቅተንም።

ይህ ሁሉ ደግሞ የሆነው ፣ ህጻናትና አዛውንቶችን ፣ መስጊድና ሆስፒታሎችን ሳትለይ በቦምብ በምትቀጠቅጣት ሳውዲ አረቢያ አማካኝነት ነው። ከዚያም በላይ የርዳታ ምግብ እንዳይገባ ወደቧን አፍና አላስገባ ባለቻት በዚህችው በሳውዲ አማካኝነት ነው።
ጋዜጠኛን ገድላ ቆራርጣና በመርዝ አሟሙታ የገደለች አገር ፣ ይህን ማድረጓ አይደንቅም። የሚደንቀው ግን ሃያላኑ አገራት እያዩ ዝም ማለታቸው ነው።

ሳውዲ አረቢያ ለሚሞቱት የመናውያን ነፍስ ሁሉ ተጠያቂ ናት። ፈጣሪ እግዚአብሔር ከየመናውያን ጋር ይሁን እርሱ በቸርነቱ ይድረስላቸው።

(ተጻፈ- በሄኖክ ተፈራ)

Share.

About Author

Leave A Reply