የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ግጭት በተፈጠረ ቁጥር ዱላ ይዞ የሚንደረደር ከሆነ የእሱ መማር ምኑ ላይ ነው?

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በአሁን ሰዓት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ የሚፈልገው፣ ይህን እውን ለማድረግ በጀት መድቦ የሚንቀሳቀሰው እና የአማራና ኦሮሞ ተወላጅ በሆኑ ተማሪዎች መካከል ግጭት በመፍጠር የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ያለማሳለስ የሚታትረው በጌታቸው አሰፋ የሚመራው ፀረ-ለውጥ ቡድን እንደሆነ ማሰብና ማስተዋል ለሚችል ሁሉ ግልፅ ነው። በተማሪዎች መካከል ጸብና ግጭት ለመፍጠር የተለያዩ አጋጣሚዎች እና ስልቶችን ይከተላሉ። ምክንያቱም ኢትዮጲያ ውስጥ ግጭትና ሰርዓት-አልበኝነት ከጠፋ፣ የዜጎች መፈናቀል ቀርቶ በሚኖሩበት አከባቢ በነፃነት መስራትና መንቀሳቀስ ከጀመሩ፣ ይህን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ከሰፈነ፣ የሁሉም ዓይንና ትኩረት ህወሓትና በህወሓት ተላላኪዎች ላይ ያነጣጥራል። የሚሸፈን ገበና፣ የሚደበቅ ቅሌት፣ የሚድበሰበስ ውርደት ውስጥ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው።

ህወሓቶች የሰው ዓይንና ትኩረት ያስፈራቸዋል፣ ያሳፍራቸዋል፣ ያስጨንቃቸዋል። ሽንፈት ያጋለጠውን ገበና፣ ቅሌት እና ውርደት ለመሸፋፈን፣ ለመደበቅና ለማድበስበስ የሚችሉት የብዙሃኑን ዓይንና ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ በማስቀየስ ነው። የቀራቸውን እድሜ የሚያራዝሙት በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ግጭትና ሁከት በማስነሳት፣ የሰውን ፍላጎትና ትኩረት ወደዛ አቅጣጫ በማዞር ነው። በአጠቃላይ ከብሔር ግጭት የፖለቲካ ትርፍ የሚያጋብስ፣ በዜጎች ሞትና ጉዳት ተቀባይነት የሚያገኝ፣ ፍርሃትና ሽብር ሲሰፍን ነፍስ የሚዘራ፣ ሀገር ለመዝረፍና ለማፍረስ አበክሮ የሚሰራ ህወሓትና ህወሓት ብቻ ነው። ስለዚህ ሁከትና ብጥብጥ፣ ግጭትና አለመረጋጋት የህወሓት ዓላማና አጀንዳ መሆኑ ምንም አያስገርምም።

የሚያስገርመው ማንበብና መፃፍ፣ ማሰብና ማገናዘብ የሚችሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የህወሓት መጠቀሚያና መገልገያ ማሳሪያ መሆናቸው ነው። እንዴት አንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ከአመት-አመት አይሻሻልም። በከልካሻ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት እንዴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እርስ-በእርሱ ተደባድቦ ይገዳደላል። ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፀብና ግጭት መፈጠሩ የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን እንደ ተማረ ሰው በሰለጠነ ተነጋግሮ ችግሩን መፍታት ሲቻል ዱላና ድንጋይ ይዞ እርስ-በእርስ ለመቀጣቀጥ መሮጥ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ፀብና አለመግባባትን በንግግር እና በውይይት ከመፍታት ይልቅ በዱላና በድንጋይ እርስ-በእርስ ለመገዳደል የሚንደረደር ተማሪ የእሱ ማወቅና መማር ምኑ ላይ ነው?

(ስዩም ተሾመ)

Share.

About Author

Leave A Reply