የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንትና ተቃዋሚያቸው ሬክ ማቻር ስልጣን ለመጋራት ተስማሙ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና ተቃዋሚያቸው ሬክ ማቻር ሀገሪቱን በጋራ ለማስተዳደር ተስማሙ። ላለፉት ሁለት ሳምንታት በካርቱምና በካምፓላ ውይይት ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ተቃዋሚው ሬክ ማቻር የምክትል ፕሬዚዳንትነቱን ስልጣን እንዲይዙ ተስማምተዋል።

ከሁለት አመት በፊት የግድያ ሙከራ ተደርጎብኛል ብለው ጁባን ለቀው የወጡት ሬክ ማቻር አሁንም መልሰው ያንኑ የምክትልነት ስልጣን መያዛቸው አስገርሟል።

የሁለቱ ስምምነት ለእዚህ ጫፍ መድረስም የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው።

ከሶስት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢጋድ በይነ መንግስታት አስቸኳይ ስብሰባ  ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እናንት ለሀገራችሁ ህዝቦች የማታስቡና ወደ ስምምነት የማትመጡ ከሆነ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የህግም የሞራልም ግዴታ አለባት” በማለት ማሳሰባቸው ይታወሳል።

Share.

About Author

Leave A Reply