የዳያስፖራ የቁጠባ ሒሳብ ያላቸው ደንበኞች መጠኑ ያልተገደበ የውጭ ምንዛሬ መቆጠብ ይችላሉ:- የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ስብሰባ አድርጓል፡፡

ኮሚቴው ከዚህ ቀደም በዳያስፖራ ቁጠባ ላይ ተቀምጦ የነበረው የ50 ሺ ዶላር ገደብ አንስቷል፡፡

በውሳኔው መሰረት የዳያስፖራ አካውንት ያላቸው ደንበኞች የፈለጉትን ያህል ገንዘብ በውጭ ምንዛሬ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡

ኮሚቴው ከዚህ ቀደም ክፍያን በውጭ ምንዛሬ እንዲቀበሉ የተፈቀደላቸው ተቋማትን በማስፋት አገልግሎታቸውን ለውጭ ደንበኞች የሚሰጡ አየር መንገድ፣ የቴሌኮም አገልግሎት፣ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ ልዩ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎችን እንዲያጠቃልል ወስኗል፡፡

ምንጭ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

Share.

About Author

Leave A Reply