የጀነራል አሳምነው ጽጌ የመጨረሻዎቹ ሰዓቶች

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

መስዋእትነት የጥልቅ እምነት መራራ ውጤት ነው። ሽንገላና ኑፋቄ የክብር ጌጥ በሆነበት፣ ህሊናውን ያስታወከ ሁሉ መንበሩን በወረረበት በዚህ ዘመን አውጥቶ አውርዶ ለተቀበለው እውነት እራሱን አሳልፎ መስጠቱ ምናልባት የቀደሙት አባቶቻችን “እኛም በዘመናችን እንዲህ ነበርን ለማለት ለምልክት ትተውልን የሄዱት ሰው ቢሆን ነው” ብለን እንድናምን ግድ ሳይለን አይቀርም፤ጀነራል አሳምነው ጽጌ።

የዛሬው አሳምነው ጽጌ የኋለኛውን ማንነት ይዞ የወጣው የሰው ልጆች የሞት ሰረገላ ከሆነው ማእከላዊ ነው። የደደቢት ጭፍሮች “አንተ ሽንታም አማራ፤ ገና ቀሚስ አልብሰን ማድቤታችን ውስጥ የወጥ ቀቃይ ነው የምናደርግህ” እያሉ ሲያስታውኩበት ከግርፊያው በላይ ከአንደበታቸው ይወጣ የነበረው ግማት እስከጥፍሩ ድረስ ዘልቆ ይጠዘጥዘው እንደነበር እናውቃለን። አሳምነውንና ጓደኞቹን ከዝዋይ እስር ቤት ለማስመለጥ ተጀምሮ ለነበረ አንድ ከፍተኛ ኦፕሬሽን እነሱን ድንበር ድረስ በመኪና ሊያደርስ የሚችል ሰው ሳይቀር ከእስካንዲኒቪያን ከገባ በኋላ አሁን እዚህ ሊገለጥ በማይችል ምክኛት እቅዱ ሳይተገበር ሲቀር የመጨረሻው ተስፋ ተሟጠጠና የነዚህ ሰዎች ህወሃት ሞቶ በህይወት ይወጣሉ ብሎ ማሰብ አቀበት የነበረበትን መራር ዘመን መርሳት አይቻልም።

ጀነራል አሳምነው ቆፍጣና ወታደር እንጅ ፖለቲከኛ አይደለም። ይልቁንም “የታገልኩት ህዝቤን የትግሬ ባሪያ፣ አገሬንም የጎተራ አይጦች መጫዎቻ ለማድረግ አልነበረም” በሚል ቁጭት እነርሱ “ከሰማይ እንደወረደ መልዓክ” የሚያዩትን መለስ ዜናዊንና ጋሻጃግሬዎቹን ለመቀንጠስ ብረቱን የወለወለ ቆፍጣና እንጅ።

ጀነራል አሳምነውን የማውረዱ ዘመቻ፤
የሴራው እርሾ ተቦክቶ የተጋግረው ጠሚሩ ደሴ በነበረበት ወቅት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። እነ አምባቸው ደግሞ እንደ ጉሽ ጠላ ተግተው ዙሪያ ገባውን አደጋ ባለማየት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ተንደርድረው ባህርዳር መጡ። ጀነራሉ የደህንነት ሰው እንደመሆኑ በእያንዳንዷ ነገር ላይ መረጃ አለው። ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደረገው ደግሞ “የዚህ ሁሉ ከበባ አላማው አማራው ለምን መሳሪያ ይታጠቃል የሚል ነው” ፣ “ፋኖን ለመበተን ነው” የሚል እምነት ስላለው ሴራውን በድፍን የአማራ ህዝብ ላይ የተነጣጠረ እንጅ እርሱ ላይ በግል የተቃጣ አደጋ አድርጎ አለመሰውዱ ነው ።

የስብሰባው ቀን የተቆረጠው በነአቢይ ለመሆኑና እያንዳንዱን እንቅስቃሴ እየተከታተሉ የጀርባ ድጋፍ ይሰጡ እንደነበር ለማወቅ አንዱ ማስረጃ ይህ ስብሰባ በተካሄደበት ቀን ከስብሰባው ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ በባህር ዳር የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦ የነበረ መሆኑ ነው።

ጀነራሉ በበኩሉ ነገሩን ሲያስብበት ከርሞ እርሱም በግሉ የደህንነት አባላቱን በተቀራራቢ ሰዓት ስብሰባ ጠርቷል። ነገር ግን ባልተለመደ ሁኔታ ሁሉም የድህንነት አባላት መሳሪያ ፈተውና ስልካቸውን እያስረከቡ እንዲቀመጡ ሲደረግ ከውጭ ደግሞ ቢሮውን በፋኖ እንዲከበብ አደረገ።

በማስከተለም የስብሰባውን አስገዳጅነት፣ “የብአዴን አመራሮች ከነአቢይ ጋር እየዶለቱ ገበሬውን ትጥቅ በማስፈታትና ፋኖን በማፍረስ አማራውን ለእርድ ሊያዘጋጁት ነውና አስፈላጊውን እርምጃ ወስደን እቅዱን ማክሸፍ አለብን” የሚል ጠቅለል ያለ ማብራሪያ ሰጠ። ሆኖም ግን ተሰብሳቢዎቹ እንኩዋን ወጥ አቋም ሊይዙ ቀርቶ ጭራሽ ተከፋፍለው ቁጭ አሉ። በዚህ መሃል ሰዓቶቹ መባከን ሲጀምሩና ሁኔታውን ወደ አንድ ሃሳብ ማምጣት እንደማይቻል የተረድው ጀነራል አሳምነው ደህንንቶቹ ከስብሰባው ቦታ ሳይወጡ በፋኖ እንዲጠበቁ ካደረገ በኋላ የተወሰነ ኃይል ይዞ ወደነ አምባቸው የመሰብሰቢያ ቦታ አመራ። ከዚህ በኋላ ማፈግፈጉ ትርጉ አልነበረውም። የመታሰርንም ክፉ ጠባሳ ጠንቅቆ ያውቀዋል።

ዚያ ላይ አማራውን ከጥቃት ለመታደግ በፋኖ ዙሪያ መገንባት ለጀመረው ኃይል አርያና ምሳሌ መሆን እንዳለበት ያውቃል። በመሆኑም እዚህ ላይ ደርሶ ቢሸነፍ ጉዳቱ ፈርጀ ብዙ ሊሆንበት ነው። ከምንም በላይ ግን ከእስር ቤት መልስ እየኖርኩ ያለሁት ህይወት ትርፍ ነው ሲል ደጋግሞ ተናግሯል። በዚም የተነሳ እጣ ፋንታውን በገዛ እጆቹ መጻፍ ጀመረ። አረሩንም አውጥቶ “የነ አብይ ተላላኪ ናቸው” ብሎ ባመነባቸው አመራሮች ላይ አርከፍክፎ ወጣ። በመጨረሻም ጎንደር መስመር ላይ ጥይቱ እስኪያልቅበት ተዋግቶ በክብር አለፈ።እውነታው በጥቅሉ ይኼው ነው። ከዚያ በተረፈ “አቢይ ባህርዳር ነበረ” እንዲሁም “አቢይ እንደ ኖህ እርግብ ጸአዳ ነበረ” የሚለው የሁለት ወገን ውዝግብ ከጭፍን ጥላቻና ከጭፍን ደጋፊነት የመነጨ በመሆኑ ለአገርም ለወገንም የሚረዳ አይደለም።

እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ነገር አሳምነው ጽጌ የመስዋእትነቱን ከፍታ ሰቅሎና በኢትዮጵያዊነት ላይ እጃቸውን ለሚያነሱ ሁሉ የገሃንምን በር ወለል አድርጎ ከፍቶላቸው እንደሄደ መጠርጠር አይቻልም።ሁለተኛው የአለም ጦርነት የተጸነሰው በአንደኛው የአለም ጦርነት ማህጸን ውስጥ ነው። የአንደኛው አለም ጦርነት ደግሞ ኢሚዲየት ኮውዝ ተብሎ የተመዘገበው ምክንያትም የኦስትሮ ሃንጋሪው መስፍን በአንድ ከሰርቢያ ናሽናሊት ፋኖ በተተኮሰ ጥይት ሳራየቮ ውስጥ መገደሉ ነበር። አለማችንንም ወደ መቶ ሚሊዮን ገደማ የሰው ህይወት ጠይቋታል።

አለማቀፍ የዜና ዘገባዎችን በተመለከተ ሁኔታውን በሙሉ “ከአማራ ገዥ መደብ የማንሰራራት ሂደት” ጋር በማያያዝ ድርጊቱን ሲኮንኑ መዋላቸውን ታዝበናል። ምድረ ፍናፍንትና ሰዶማዊ ሁሉ በዚህ ደረጃ ድርጊቱን ማጦዛቸው “እኛ የቆሻሻ መድፊያ አይደለንምና መሬታችንን መርገጥ የሚታሰብ አይደለም” ሲል ጀነራሉ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወሰዶት በነበረው አቋም እንጀታቸው ቢቃጠል ነው። መስቀሉ አየለ 

Share.

About Author

Leave A Reply