የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ለ45 ኢትዮጵያዊያን ምህረት አደረጉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኡማር ጊሌ በተለያዩ ወንጀል ተከሰው ከ አንድ እሰከ 10 ዓመት ተፈርደባቸው በጅቡቲ ማረሚያ ቤት ለነበሩ 45 ኢትዮጵያዊያን ምህረት አድርገውላቸዋል።

የኢፌዲሪ ጠ/ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ በጅቡቲ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ እና የረማዳን በዓል ምክንያት በማድረግ ፕሬዝዳንቱ ምህረት አድርገውላቸዋል።

በጅቡቲ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በይቅርታ የተፈቱትን ኢትዮጵያዊያንን ተቀብሎ እያስተናገዳቸው ሲሆን አስፈላጊው የጉዞ ሰነድ ተዘገጅቶላቸው በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤምባሲው አማካኝነት ከአገሪቱ የውጭ ጉዳይና የፍትህ ሚኒስቴሮች ጋር ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት

 

Share.

About Author

Leave A Reply