የግብፅና የሱዳን መሪዎች በቀጣናዊ ስጋቶች ዙሪያ ተወያዩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ ከሱዳኑ አቻቸው ኦማር ሀሰን አልበሺር ጋር በቀጣናዊ ስጋቶች ዙሪያ ትናንት ምሽት ካርቱም ላይ ተወያይተዋል።

ፕሬዚዳንት አል ሲሲ በሱዳን የሁለት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።

መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማሻሻል፣ የጋራ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እና ቀጣናዊ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ማድረጋቸው ነው የተነገረው።

የቀይ ባህር የፀጥታ ሁኔታ፣ ቀጣናዊ ስጋቶች፣ የደቡብ ሱዳን ሰላም እና የሊቢያ ቀውስም የውይይት አጀንዳ ነበሩ ተብሏል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድና የጉዞ ስራዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ችግሮችን በሙሉ ለማስወገድ ሁለቱ መሪዎች መስማማታቸውን አልበሺር ተናግረዋል።

አልሲሲ ከአልበሺር ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት የእሳቸው ጉብኝት በሁሉም የትብብር መስኮች ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን ለማሳካት ነው።

ምንጭ፦ aawsat.com

 

Share.

About Author

Leave A Reply