የግንቦት ሰባት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የግንቦት ሰባት አመራሮች አይሰራም ያሉት የሰላማዊ ትግል በከፈተላቸው በር፣ በቅርብ ወደ አዲስ አበባ በቦሌ በኩል ይገባሉ። ለዶ/ር ብርሃኑ ከፍተኛ አቀባበል ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ ወጭ ተለቋል።

ግንቦት ሰባት ላለፉት ስንት አመታት በትጥቅ ትግል ስም የሰበሰበው ከፍተኛ የገንዘብ አቅም አለው። የፖለቲካ ብቃት ያላቸው ብዙ አመራሮች ያሉት ድርጅት ነው። ሆኖም ግን ቁጥሩ ቀላል በማይባል ማህበረሰብ ዘንድ ፣ ላለፉት በርካታ አመታት ሲነዙት በነበረው የዉሸት ፖለትካ ምክንያት ተቀባይነታቸው ተጎድቷል። በተለይም በአማራው ክልል።

ያንን ተቀባይነት መልሰው ማምጣት ይችላሉ ፧ ይችላሉ ባይ ነኝ። በተለይም ፡

አንደኛ – የፖለቲካ ፕሮግራሞቻቸው ከበፊት ቅንጅት ብዙ የተለወጠ ካልሆነና አሁን ያለውን የጎሳ ፌዴራሊዝም ማፍረስና በተሻለ ፌዴራሊም መተካት አለበት የሚል አቋም ከያዙ፣

ሁለተኛ አዲስ አመራር ወደፊት በማምጣት ነባሮቹ አመራሮች በአማካሪነት እንዲሰሩ ቢያደረጉ

ሶስተኛ – ድርጅታቸው ያለ ምንም መሸራረፍ ውስጣዊ ዲሞክራሲ ኖሮት ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ድርጅት ከሆነ

አራተኛ – አገር ቤት ካሉ ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ፓርቲዎች ጋር በጋራ፣ በመከባበር ቢሰሩ

ትልቅ አስተዋጾ ሊያበረክቱ ይችላሉ።

ግርማ ካሳ

Share.

About Author

Leave A Reply