የጎሳ ፌደራሊዝም ለመተላለቅ እያዘጋጀን ነው – ገለታ ጋሞ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የጎሳ ፌደራሊዝም ለመተላለቅ እንድንዘጋጅ የተወጠነ እንጂ ሰላም ለማምጣት የተወጠነ አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ሕዝብ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየፈለሰ አንዱ ከሌላው እየተዳቀለ፣ አንዱ አንዱን በወረራ እየያዘ ለሺዎች ዓመታት በኖረበት አገር ይህ ግዛት የኔ ነው ለማለት የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ ያለው ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም።

የኦሮሞን ጉዳይ ብንመለከት ዛሬ ኦሮምኛ የሚነገርባቸው አካባቢዎች ከ90% በላይ የዛሬ 300 ዓመት ኦሮሞ አልነበረባቸውም። ወይም በሌላ አነጋገር አሁን የሚኖረው ህዝብ የገዢዎቹን ቋንቋ ኦሮምኛ ይናገራል እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ከእውቀት ማነስ ዛሬ ኦሮሞ የሚመስለው ሰው ቢኖርም።

የጅማ ህዝብ እናሪያ፣ የምና ዳውሮ ነው። ኦሮሞው የገዢ መደቦቹ ብቻ ነበሩ። የወለጋ ህዝብ ማኦ ማኦና ሌሎች ኦሞቲክ ዘሮች ናቸው። በሕዝቡ ላይ መጥተው ባላባት የሆኑት፣ ባሪያ አድርገው የሸጡት ናቸው ኦሮሞዎች። የአርሲ ሕዝብ ሃዲያ ነው። የሸዋ ሕዝብ ጋፋት ነው።

በአማራው በኩል የጎጃምና ጎንደር ሕዝብ አገውና ቅማንት ነው። አማራ ነኝ ብሎ ከቅማንት ጋር ሲቧቀስ ያስቃል። የወልቃይት ህዝብ ትግሬ የሚል ስም ከመኖሩ በፊት የነበረ ነው።

እነዚህን እወነቶች ደብቆ በማቆየት ብቻ ነው የጎሳ ፌደራሊዝምን መተግበር የሚቻለው። ደብቆ እስከመቼ?

ይህም ሆኖ ሰላማዊ ሁኔታ አይፈጠርም። አማራ ነኝ የሚለው እስከ ዝዋይ ድረስ ግዛቴ ነው እያለ ነው። ኦሮሞ ነኝ የሚለው፣ ወሎ ድረስ ግዛቴ ነው እያለ ነው። ወልቃይት ራያ ጦርነት አፋፍ ላይ ነው ያለው። ሶማሌውና ኦሮሞው መሃከል ያለው የግዛት ጥያቄ መቼም ቢሆን አይፈታም።

አሁን ያለው የፌደራል ስርዓት ድምጥማጥ ለሚያጠፋን ጦርነት እያዘጋጀን እንደሆነ ማየት የሚሳናቸው ህልመኞች ብቻ ናቸው።

Share.

About Author

Leave A Reply