የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክረ ሀሳብ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የ2011 የፌደራል መንግስት በጀትን በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፥ በአዲሱ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ጤነኛ ኢኮኖሚ እንደትይዝ ያግዛል ያሉትን ምክር ሀሳብ አቅርበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ሀሳብ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ዜጎች የበኩላቸውን አስተዋፀኦ ለሀገራቸው ማበርከት የሚችሉበትን መንገድ የዘረዘረ ነው።

ዲያስፖራ

በተለያዩ አለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ዲያስፖራዎች የሚልኩትን ዶላር በባንክ ብቻ ሊያደርጉ ይገባል።

ይህም ህገ ወጥነትን ለመከላከልና ለመቀነስ እና በሀገር ደረጃ የተያዘውን ፍላጎት ለመመለስ ይረዳል።

ለዚህ ራሱን የቻለ ተቋም ማቋቋም የሚቻል ሲሆን፥ በዚህ ተቋም ዲያሰፖራዎች ከቀን ወጪያቸው አንድ ዶላር እንዲያስቀመጡ ይደረጋል።

በዚህም በሀገር ውስጥ ያለውን የልማት ስራ ለማከናወን ያስችላል፤ በማለት በትንሹ በየቀኑ በሀገሪቱ አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት እንደመገንባት መሆኑን አንስተዋል።

ይህን ካላደረገ ሌቦችን እየጠቀመ ደሃን እየጎዳ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባልም ነው ያሉት።

ወጣቶች

በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው እና ይህንንም ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል።

በክረምት ወቅት ነፃ አገልግሎትን በመስጠት ለኢኮኖሚው አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ምሁራን

ምሁራን ባላቸው እውቀት የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲጠናቀቁ ድጋፍ እንዲያደርጉ እና ወጣቶችን በመቅረፅ በኩል በክረምት ወቅት የሀሳብ እና የእውቀት ድጋፍ ማቅረብ ይገባቸዋል።

ባለሀብቶች

ባለሀብቶች ያላቸውን እውቀት በመጠቀም ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ማስፋፋት ይጠበቀባቸዋል።

ግብርን በመክፈል የሀገር ገቢ ማሳድግና፣ ባልተገባ የንግድ ስራዓት አለመነሰማራት እና ሀብት ማሸሸት ማቆም ይኖርባቸዋል።

የመንግስት ሰራተኞች

የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ሌብነትን በመጠየፍ፣ ያልተገባ አሰራርን በማቆም አሁን የሚታየውን የሀብት ውስንነት መቅረፍ ይቻላል የሚል ሀሳብን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀምጠዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply