የጨፌ ኦሮሚያ 8ኛ መደበኛ ጉባዔ ከሃምሌ 2 ጀምሮ ይካሄዳል

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጨፌ ኦሮሚያ 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሀምሌ 2 እስከ ሀምሌ 4/2010 በአዳማ ጨፌ አዳራሽ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

ጨፌው በሚቀርቡለት አጀንዳዎች ላይ በቡድን ደረጃ ከሰኔ 30 እስከ ሀምሌ 1/2010 ድረስ ውይይት ያደርጋል ነው የተባለው፡፡

ለጨፌው ውይይት ከሚቀርቡ አጀንዳዎች መካከል፡-

የስራ አስፈጻሚ አካላት የ2010 አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2011 እቅድ
የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች የ2010 አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2011 እቅድ
የኦሮሚያ ኦዲት መስሪያ ቤት የ2010 አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2011 እቅድ
የጨፌ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት የ2010 አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2011 እቅድ
የ2010 በጀት ዓመት የበጀት ጭማሪ አዋጅ
የ2011 በጀት ዓመት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጀትና
የተለያዩ ሹመቶችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Share.

About Author

Leave A Reply