የፌደራል መንግስት የ2011 በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግስት የፌደራል መንግስት የ2011 በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ።

ምክር ቤቱ በትናንትናው እለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የ2011 በጀት ላይ በዝርዝር መወያየቱም ይታወሳል።

ዛሬም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት በዝርዝር ተወያይቷል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2011 ዓ.ም በጀት 346 ቢሊየን 915 ሚሊየን 451 ሺህ 948 ብር ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 91 ቢሊየን 67 ሚሊየን 160 ሺህ 588 ብር እንዲሁም 113 ቢሊየን 635 ሚሊየን 559 ሺህ 980 ብር ደግሞ ለካፒታል ወጪ የተመደበ ነው።

ከዚህ ባለፈም 135 ቢሊየን 604 ሚሊየን 731 ሺህ 380 ብር ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ደግሞ 6 ቢሊየን ብር ተመድባል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply