የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብርና መጠኑ ያልታወቀ ዶላር ዘርፈዋል የተባሉ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና ማርያም አካባቢ የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስን በመልበስ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብርና መጠኑ ያልታወቀ ዶላር ዘርፈዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ ግለሰቦቹ በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

ከላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው፥ ተጠርጣሪዎቹ በትናንትናው እለት በላፍቶ ክፍለ ከተማ ሃና ማርያም ተብሎ በለሚጠራው አካባቢ ከቀኑ ስድስት ሰአት ላይ ነው ዝርፍያውን የፈፀሙት።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ዝርፊያው በሚፈፀምበት ጊዜ አንድ ግለሰብ ያሰማውን የድረሱልኝ ጩኸት ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለፖሊስ ባደረጉት ጥቆማ ነው።

ፋና

Share.

About Author

Leave A Reply