የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ እና መስመሮች ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለፀ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የከተማዋ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ እና መስመሮች ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለፀ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅና የፍሳሽ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዓለም ባዩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የቤት ውስጥ ፍሳሽ ቆሻሻን ብቻ ለማጣራት በተገነባው ማጣሪያ ጣቢያና የፍሳሽ መስመሮች ውስጥ በሚገቡ ደረቅ ቆሻሻዎች፣ የዝናብና ጎርፍ ዉሃ፣ ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የሞተር ዘይት፣ ኬሚካል፣ስብና ቅባቶች እንዲሁም ሌሎች ተረፈ ምርቶች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ይገኛሉ።

የፍሳሽ ማጣሪያዎች ባዕድ ነገሮች እንደ ጆንያ፣ ላስቲኮች፣ ፀጉርና ላባ፣ ዳይፐር፣ ጨርቃጨርቆች፣ ደረቅ ቆሻሻዎች፣ ጠጠር፣ አሸዋ፣ አፈርና መሰል ነገሮች ወደ ማጣሪያው እየገቡ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኙ ሃላፊው ገልፀዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህን አውቆ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ወጥቶባቸው የተገነቡ የፍሳሽ መሰረተ ልማቶችን ከአደጋና ከብልሽት በመጠበቅ፣ ከመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ቆሻሻ ውጪ ሌሎች ጠጠርና ፍሳሽ ነገሮች ወደ መስመር እንዳይገቡ ጥንቃቄ በማድረግና ለፍሳሽ መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

EPA

Share.

About Author

Leave A Reply