“ዮ”ን ፍለጋ በኢቢኤስ የቀረበው ዝግጂት “ከመጋረጃ ጀርባ” ቴያትር ላይ የተሰረቀ ነው ተባለ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

(ቶፊቅ ኑሩ)

“አርብቶ አደሩ” የቴሌቭዥን ጣቢያ EBS እጅግ ተወዳጅ፣አነጋጋሪና የዘመኑ ምርጥ ከሆነው “ከመጋረጃ ጀርባ”ቴአትር ላይ ለወሬ በማይመች መልኩ ከተኮናተራቸው “አሙቁልኝ አርቲስቶቹ”ጋር በማበር በአደባባይ፤በሚሊዮኖች ፊት አሳፋሪ ዘረፋ መፈፀሙ ይታወቃል። ይህን በተመለከተ ፕሮግራሙ ከመተላለፉ በፊት ማስታወቂያውን ተመልክታችሁ ለጠቆማችሁን፣ እየተላለፈ ሳለና አየር ላይ ከዋለ በኃላ ሀዘናችሁን፣ ተቆርቋሪነታችሁንና ኡኡታችሁን ለገለፃችሁልን የጥበብ ቤተሰቦች፣ጋዜጠኞች፣ እውነተኛ አርቲስቶቻችንና ወዳጆቻችን ምስጋናችን ይኸው!
በሀሳብ ድርቀትና በፈጠራ እጥረት ሠርክ የሚታማው ከላይ የገለፅኩት ምንትስ ቲቪ ከአርቲስት ተብዬዎቹ ጋር በመቧደን፣ ነጥብ እንኳ ሳይቀር ባላዋቂነት እንደሚኮርጅ ሠነፍ ተማሪ የ”ከመጋረጃ ጀርባ”ን ደራሲ የአዕምሮ ፈጠራ አራቁተው ገልብጠዋል። የሌባ አይነ-ደረቅ እንዲሉ አይኖቻቸውን በጨው አጥበው ሚሊዮኖች ፊት ሲቀርቡ ለዓመል ያህል እንኳ አላፈሩም፤ቅንጣት ታህል አላመዛዘኑም። ማጅራት መቺ ሌባ እንኳ አሳቻ ሠዓትና ቦታ ጠብቆ ለሚዘርፈው ሠው መለ-መላውን መሸፈኛ ፓንት ያስቀርለታል። ሌብነትም የራሱ “ጥበብ”ና ልክ አለዋ! እነዚህ እኮ ጉዶች ናቸው! ሠው እንዴት ከሀ-ፐ ማጅራት ይመታል? ሙሉ ታሪክ ከነቃለ-ተውኔት በአደባባይ ይዘረፋል? ምናለ መዝጊያ ሙዚቃውን እንኳ ቢቀይሩት!
ትሰሙኛላችሁ እነእንቶኔ! በደራሲው፣በአዘጋጁ፣ በተዋንያኑ፣ በሌሎች የቴአትሩ ባለሙያዎች፣በሀገር ፍቅር ቴአትር…በአጠቃላይ በኪነ-ጥበብ ላይ በንቀት የፈፀማችሁት ይህ ግፍና ዝርፊያ አሳፋሪ ተግባር ነው ተብሎ አይታለፍም። እኔ፣የቴአትሩ ባለሙያዎች፣ሀገር ፍቅር፣ጋዜጠኞችና ሌሎች የጥበብ ተቆርቋሪዎች ህጋዊ መስመሩን ጨምሮ በየትኛውም መንገድ እንፋለማችኃለን! በንቀታችሁ ልክ እንፋረዳችኃለን! “ብለቅሽ ወገቤ ይላቀቅ”ያለው ማን ነበር?

Share.

About Author

Leave A Reply