ድሬደዋ የአፓርታይድ አፈጻጸም ቀመር ስለወጣባት እንጂ ከሌሎች ክልሎች በእጅጉ የተሻለች ናት

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ድሬደዋ የአፓርታይድ ህጉ ሁነኛ ማሳያ ከመሆኗ በስተቀር ከሌሎች ክልሎች በእጅጉ የተሻለች ናት

ኢትዮጵያ ላለፉት ሀያ ሰባት አመታት በአፓርታይድ ህገ መንግስት ለመመራቷ ጥሩ ማሳያው የድሬዳዋ ከተማ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ክፍፍሉን በ40+40+20 ቀመር ማስቀመጧ ነው።

የህወሀት/ኢህአዴግ ፍጹም ነውረኛ የሆነውና በአፍሪካ ብቸኛው የሆነው የብሄር ህገ-መንግስት የኢትዮጵያን ህዝቦች በመከፋፈል ያንተ የኔ የሚል የጎጥ ፖለቲካ እንዲያራምዱና ሲብስም እርስ በእርስ እንዲገዳደሉበት ሰበብ ሆኗል።

ድሬ (የፍቅር ሀገር) ደግሞ ቀድሞ በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባት ዜጎች የብሄር ጀርባቸው እየተጠና በከተማዋ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን አንድም ኦሮሞ አልያም ሶማሌ መሆን ይጠበቅባቸው ነበር – ለሀያ ሰባት አመታት።

ይሁን እንጂ ይህ ድሬደዋን የተሻለች ሚዛናዊ መሆኗን ያስይ እንደሆን እንጂ በክፉ የሚያስነሳት ጉዳይ አይደለም። ትግራይ ክልል እኮ መቶ በመቶ የትግሬ ብሄር ካልሆነ ወደ ፖለቲካ ስልጣንም ሆነ ወደ ኢኮኖሚ ውድድር ሊመጣባት አይችልም። ኦሮሞ ክልልም ቢሆን ኦሮሞ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ወደ ጨፌ ኦሮሚያ የፖለቲካ መድረክ ሊጓዝም ሆነ በክልሉ ውስጥ ያለ የኢኮኖሚ ገጸ በረከት ተቋዳሽ አይሆንም። አማራ ክልልም ብንሄድ እንዲሁ ነው። ደቡብም ሶማሌም፣ ቤኒሻንጉልም..ብቻ ሁሉም ክልል የራሱን የደም ማጥራት ስራ ሰርቶ እንጂ እንዲሁ በኢትዮጵያዊነት ብቻ የሚሰጥ ስልጣን ወይም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የለም።

እናም ድሬደዋ ነገሩ ጎልቶና አይን አፍጥጦ በሂሳብ ቀመር፣ ኦሮሞና ሶማሌ በፈረቃ የሚገዙት ስልጣንና የሚቦጠቡጡትን የሀብት ክፍፍል ተደረገላቸው እንጂ ነገር በመላው ሀገሪቱ ከክልል እስከ ዞን፣ ከዞን እስከ ልዩ ወረዳ፣ ከቀበሌ እስከ ጎጥ የአካባቢው ተወላጅ የሚባለው በብሄር ተኮር የቋንቋ ሚዛን እንጂ በኢትዮጵያዊ ማንነት አይደለምና የድሬዳዋው የተለየ ነገር አለው ለማለት አያስደፍርም።

እናም መፍትሄው በድሬ ጉዳይ ለይቶ መሟገት ሳይሆን በሀገራችን ባይተዋር ያደረገንን የአፓርታይድ ህግ መፈልፈያ የሆነውን ህገ-መንግስት መቀልበስ ብቻ ነው

Share.

About Author

Leave A Reply