ድንገተኛ የእሳት አደጋ በጅማ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

በጅማ ከተማ የተነሳ #ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የጅማ ከተማ ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽህፍት ቤት አስታወቀ።

ንብረትነቱ የሦስት ሰዎች የሆነ አንድ ህንጻ መሳሪያ መሸጫ ሱቅ በእሳቱ ሙሉ ለሙሉ ቢወድምም ወደሌላ ከመዛመቱ በፊት በቁጥጥር ስር መዋሉን በጽህፍት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ሳጅን ሀዊ አልይ ለኢዜአ ተናግረዋል።

እንደምክትል ሳጅን ሀዊ ገለጻ የእሳት ቃጠሎው የተከሰተው ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚካሄድበትና በተለምዶ “አረቦች ተራ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

የእሳት ቃጠሎው የተከሰተው ከትላንት በስቲያ ሌሊት 8፡00 አካባቢ ሲሆን ህብረተሰቡና የከተማው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያ ጽህፈት ቤት እሳቱን ለማጥፋት ባደረጉት ርብርብ ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡

ምክንያቱ ለጊዜው ባልተወቀ ምክንያት በተከሰተው የእሳት አደጋ 2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙን ተናግረዋል፡፡

ሳጂን ሀዋ እንዳሉት እሳት በተነሳበት አካባቢ በርካታ ሱቆች የሚገኙ ቢሆንም እሳቱን ለመቆጣጠር ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በተደረገ ርብርብ እሳቱ ወደሌሎች ሱቆች ሳይዘመት በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡

ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም የገለጹት ምክትል ሳጂን ሀዊ ህብረተሰቡ በእዚህ በኩልም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእሳት አደጋው ንብረታቸው ከወደመባቸው ሦስት ሰዎች መካከል አቶ አብዱራህማን ከማል በእሳት ቃጠሎው ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ መውደሙንና በእዚህም ሀዝን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።

“ሌሊት 10፡15 አካባቢ በቦታው ስደርስ የእሳት አደጋ መከላከያ አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን እሳቱን ሲያጠፉና ወደሌላ ሱቅ እንዳይዛመት ጥረት ሲያደርጉ ተምልክቻለሁ” ብለዋል፡፡

“እኔ ሱቄን ዘግቼ ወደ ቤቴ የሂድኩት ምሽት 12፡00 ሰዓት አከባቢ ነው፤ በወቅቱ መብራት እንዳጠፋሁም አስታውሳለሁ” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ena

Share.

About Author

Leave A Reply