ዶክተር መረራ ጉዲና የብሮድካስት ባለስልጣን የቦርድ አባል በመሆን በፓርላማው ተሾሙ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 6ኛ ልዩ ስብሰባው እያካሄ ይገኛል፡፡

ምክርቤቱ 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 34ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ለህገመንግስቱ ታማኝ የሆኑ፣ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ፣ በዳኝነት በቂ ልምድ ያላቸውና ጥሩ ስነምግባር ያላቸውን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 41 ወንድ እና 8 ሴት በጠቅላላ 49 እጩ ዳኞች እንዲሁም ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 58 ወንዶች እና 16 ሴቶች ዳኞች በአጠቃላይ በ74 እጩ ዳኞች በአጠቅላይም 123 እጩ የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞች ሆነው ተሹሟል፡፡

ዛሬ ሹመት የተሰጣቸው ዳኞችም በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለመሃላ ፈጽመዋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተጓደሉ የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ለመሾም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባላትን ለመሾም የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

በዚህም ምክር ቤቱ በተጓደሉት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባላት ምትክ አቶ አህመድ ሽዴ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትር የቦርድ ሰብሳቢ፣ ዶክተር መረራ ጉዲና እና ወይዘሮ ሃሊማ ባድገባ አባል ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።

 

Share.

About Author

Leave A Reply