ዶክተር አብይ እና ጎንደር – ደህንነቶች ወደ ስብሰባው የሚገቡ ሰዎችን በመለየት ላይ ናቸው።

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላያችን ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ጎንደር አቅንተው ህዝብ እንደሚያወያዩ ዜናውን ማስነገራቸው ይታወቃል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት በሚል ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት፤ ከብሔራዊ ደህንነት ቢሮ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲቪዚዬን፤ ከፌደራል ፖሊስ፤ ከመከላከያ ተወከልን ብለው ከኮማንድ ፓስቱ ጋር የተቀናጁ ጎንደር ገብተው ከአቶ በለምነህ መኮንን አስተባባሪነት ከብአዴን ጽ/ቤት መመሪያ እየሰጡ ወደ ስብሰባው የሚገቡ ሰዎችን በመለየት ላይ ናቸው።

አላማውም የወልቃይት ጥያቄ ፈፅሞ እንዳይነሳ ለማድረግ እና ጠቅላዩ ላይ ምንም አይነት የተቃውሞ ድምፅ እንዳይሰማ ለማድረግ ያለመ ነው። ታስረው የነበሩ ሰዎችና ከእነሱ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚገመቱ ሁሉ ዝር እንዳይሉ አቋም ተይዟል። ጥብቅ ክትትል ከማድረግ ባሻገር ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ ተብለው የተጠረጠሩትን ሁሉ አስቀድሞ ከማሽማቀቅ ባሻገር የተወሰኑ ወጣቶችን በማሰር ለማደናገጥም መታቀዱ ታውቋል። የወልቃት የማንነት ጠያቂ ያነሱ የኮሚቴው አባላት ወደ ውይይት አደራሽ እንዳይገቡ ይደረግ መባሉን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ንጉሱ ጥላሁን በመቃወማቸው ውዝግብ መነሳቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ዋናውና አደገኛው ነገር የደህንነቱ ኃይል የቅማንት ማንነት ጥያቄ እንደገና ለአብይ እንዲቀርብ ወደ ሱዳን የሚያገናኙ 3 ቀበሌዎች ወደዛው ልዩ ወደሚሉት ዞን እንዲካተት ለማድረግ ጥያቄውን በይፋ እንዲያነሱ ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ በጎንደር ቆይታው ለብቻቸው እንዲያናግራቸው ሁኔታው እያመቻቹ መሆኑም ተጠቁሟል። አጠቃላይ ሴራው እንደተጠበቀ ሆኖ ጠቅላይ ሚንስተሩ ሺዎች የተሰውለትን የወልቃይት ጉዳይ በተራ የቃላት ጫወታ ለመሻገር እና ህወሓትን ለማስደሰት የሄደበት እርቀት ያስነሳውን ቁጣ ለመሸፈን፤ አዳራሽ ውስጥ የተመረጡ ካድሬዎች በማስገባት እንደ መቀሌው አይነት ጭብጨባ ለማሰማት በትጋት እየሰሩ መሆኑን የማያወላዳ ተጨባጭ የውስጥ መረጃ አመልክቷል።

(ሀብታሙ አያሌው)

Share.

About Author

Leave A Reply