ዶ/ር ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር በስልክ ተወያዩ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡

በዚህ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች የኀዘን መግለጫ ተለዋውጠዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠንካራ ተቋም መሆኑን የገለጹ ሲሆን ሀገራቸው አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ሁሉ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት ለተካሄዱ ሁሉን አቀፍ ለውጦች ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል።

እንዲሁም መሪዎቹ በሀገራቱ መካከል ያለውን ረጅም ጊዜ የዘለቀ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ማስማማታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

EPA

Share.

About Author

Leave A Reply