ጀነራሎቹ ይዘርፋሉ፤ ጋዜጠኞቹና አርቲስቶቹ ይዘፍናሉ

Google+ Pinterest LinkedIn Tumblr +

ከሜቴክ የሙስና ቅሌት ጋር ተያይዞ ‘አርቲስት ዝናህ ብዙ ፀጋዬ፣ ፍጹም የሺጥላ፣ ተስፋዬ ሰብስቤ እና አቤራ ኪነ ጥበባት ድርጅት በትግሉ ወቅት የነበሩ ዘፈኖችን በአዲስ መልክ ለመስራት በማለት በአጠቃላይ 1ሚሊየን 525ሺህ 208 ብር ከ04 ሳንቲም ከሜቴክ ወጭ ተደርጎ ትከፍሏቸዋል ተብሏል
——-

“ጋዜጠኛ” ፍፁም_የሺጥላ ከጄ/ል #ክንፈ_ዳኘው ጋር በሙስና ወንጀል ተጠርጥራ መታሰሯን ስሰማ ገርሞኛል፡፡ “እንዴት ጋዜጠኛ ከሀገር ከዘረፈ ጄኔራል ጋር በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ይታሰራል?” አልኩና “ፍፁም የሺጥላ ETV” የሚሉት ቃላት ለGoogle ሰጠሁት፡፡ አጅሬ ደግሞ DireTube ከሁለት አመት በፊት ያቀረበውን ዘገባ ጎልጉሎ አወጣልኝ፡፡ “የብሩህ_ኢትዮጵያ_ልጆች_ዘጋቢ_ፊልም ተመረቀ!” በሚል ርዕስ የቀረበው ዘገባ <<በትምህርታቸው ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎች በብረታ_ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አሻራቸውን እያጣለ ከሚገኙት #ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ የህዳሴው ግድብ ግንባታ፣ የአዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ኢንዱስትሪ፣ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሽን፣ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ #የሚሰሩትን_ስራ #ለተማሪዎቹ_ትምህርት #እንዲቀስሙ የሚያደርግ ዘጋቢ ፊልም ሲሆን ፊልሙንም ለመስራት የአመት ጊዜ እንደፈጀ የፊልሙ #ዋና_አዘጋጅ የሆነችው ጋዜጠኛ #ፍፁም_የሺጥላ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፃልናለች!>> ይላል፡፡ ወዳጆቼ… ላለፉት አመታት #ሜቴክ ሀገሪቷና ህዝቡን እንዴት ሙጥጥጥ… አድርጎ እንደዘረፈ ሰሞኑን ሰምታችኋል፡፡ ስለዚህ ጄ/ል ክንፈ ዳኘው ይዘርፋል፣ ፍፁም የሺጥላ ደግሞ ዘረፋውን #ዘፈን አስመስላ ዘጋቢ ፊልም ትሰራለች፡፡ እሱ ሀገር ይዘርፋል! እሷ ውሸት ትዘግባለች! እሱ ሲታሰር እሷም አብራ ገባች!!
(ሀተታው የስዩም ተሾመ ነው)

Share.

About Author

Leave A Reply